ከ4 ጨዋታዎች በኋላ ከ3 ነጥብ ጋር ለመገናኘት ካለመው አስቶን ቪላ ጋር የሚገናኙበት ተጠባቂ ጨዋታ፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት የማጠናቀቂያ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4፡00 በቪላ ፓርክ ሲካሄድ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ከአስቶን ቪላ ይገናኛል።
ከአምና ሻምፒዮንነት መልስ አዲሱን ዓመት ኮቨንትሪ ሲቲን 3 ለባዶ በመርታት በድል የጀመሩት መድፈኞቹ ምሽት ላይ በሊግ ቆይታቸው ከሚፈትኗቸው ክለቦች መካከል አንዱን ይገጥማሉ።
የኡናይ ኢምሬው አስቶን ቪላ በክረምቱ በአውሮፓ ክለቦች የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍጻሜ ጨዋታ በፓሪስ ሴንት ዤርሜን የደረሰበትን እና በፕሪሚየር ሊጉ መጀመሪያ በብራይተን የደረሰበትን ሰፊ ሽንፈት ጨምሮ ባለፉት 4 ጨዋታዎች ከድል ጋር አልተገናኘም።
እናም ዛሬ የዓመቱን የመጀመሪያ ድል ለማግኘት ከሊጉ ሻምፒዮኖች ጋር ይጫወታሉ።
ለሚኬል አርቴታው አርሰናል ብሩኖ ጉማሬሽ በኮሚዩኒቲ ሽልድ ጨዋታ ላይ በደረሰበት የጡንቻ ጉዳት ምክንያት የመጀመሪያው የሊግ መርሐግብር ያመለጠው ሲኾን ዛሬ ምሽት ግን የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ሊያደርግ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አዲሱ ፈራሚ ኢዝሪ ኮንሳ የቀድሞ ክለቡን ሊገጥም እንደሚችልም አሠልጣኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።
ከ2019/20 የውድድር ዓመት በኋላ ተከታተይ 2 የሊግ ጨዋታዎችን ላለመሸነፍ በሜዳቸው አርሰናልን የሚጋብዙት ቪላዎች አሁን በጉዳት እና በቅጣት ምክንያት የሳሳው የቡድን ሥብሥብ ይፈተናል ተብሎ ተገምቷል።
በቪላ በኩል ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል ጆን ማጊን ይገኝበታል።
ሁለቱ ስፔናዊያን አሠልጣኞች ሁሌም በተገናኙ ቁጥር መልሶ ማጥቃትን ከኳስ ቁጥጥር የሚያገናኘው እና ጠንካራ ፉክክር የሚታይበት ጨዋታቸው ዛሬም ምሽት 4፡00 ላይ ይጠበቃል።
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



