በሊጉ መክፈቻ በሀል ሲቲ 2 ለ 0 የተሸነፈው ዩናይትድ 12 ሰዓት ከ 30 ላይ በሜዳው ሌላውን አዲስ አዳጊው ቡድን ኢፕስዊች ታውንን ያስተናግዳል።
ኢፕስዊች በመክፈቻው ሰንደርላንድን ያሸነፈ ሲሆን ዛሬም ለ ማንችስተር ዩናይትድ ቀላል አይሆንም።
ማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ የውድድር አመት ነጥቡን ፍለጋ ትግል የሚያደርግበት የኦልድትራፎርድ ፍልሚያ ነው።
10 ሰዓት ላይ ደግሞ ቼልሲ ከብራይተን ይገናኛሉ። ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ መክፈቻ አሸንፈዋል።
ሊድስ ከብሬንትፎርድ እና ፉልሀም ከ ሰንደርላንድ ሌሎች 10 ስዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
መለሰ ግዛቸው



