ለኔይማር ጁኒየር የስንብት ጨዋታ ሊዘጋጅለት ነው።

0
79
የ34 ዓመቱ ኔይማር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን ተከትሎ ነው የብራዚል እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የስንብት ጨዋታ ለማዘጋጀት ማጤን የጀመረው።
“ሴሌሳዎቹ ጋር የነበረኝ ጊዜ አክትሟል፤ ደሜን እና ሕይወቴን ሰጥቻለሁ፤ ለቢጫው መለያ ታግያለሁ በዚህም ደስተኛ ነኝ፤ አሁን ግን በቅቶኛል” ብሏል ኔይማር።
ለሳንቶስ እየተጫወተ የሚገኘው ኔይማር ምንአልባት ሙሉ ለሙሉ እግር ኳስ ሲያቆም ሌላ የስንብት ጨዋታ ሊደረግ እንደሚችልም ያሆ ስፖርት በዘገባው ጠቁሟል።
በ4 የዓለም ዋንጫዎች ላይ የተሳተፈው ኔይማር በ130 ጨዋታ 80 ግቦችን በማስቆጠር የምንጊዜም ግብ አስቆጣሪ ታሪክ ጽፎ ነው ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ያገለለው።
በንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here