በኢትሀድ ያልተወደደው ካልቪን ፍሊፕስ

0
71
በዩሮ 2020 ለሦሥቱ አናብስት እና ለሊድስ ዩናይትድ ባሳየው ጥንቅቅ ያለ አቋም “የዮርክሻየሩ ፒርሎ” የሚል ቅጽል በደጋፊዎች አግኝቷል ካልቪን ፍሊፕስ።
በወቅቱ የፈርናንዲንሆ ምትክ ያሳሰባቸው ፔፕ ጋርዲዮላም ትክክለኛው ሰው ተገኘ ብለው በ42 ሚሊዮን ፖውንድ እና በ150 ሺህ ፖውንድ ሳምንታዊ ደመዎዝ አስፈረሙት።
ኾኖም ፈርናንዲንሆን ያስረሳል የተባለው እንግሊዛዊ በጉዳት፣ በአካል ብቃት ችግር እና በጨዋታ ዘዴ አለመጣጣም በኢትሀድ መክኗል።
ፍሊፕስ ለማንቸስተር ሲቲ ስድስት ጨዋታዎችን ብቻ ቋሚ ኾኖ የጀመረ ሲኾን 26 ጨዋታዎችን ተቀይሮ በመግባት ተጫውቷል።
የ30 ዓመቱ አማካኝ በቂ የመሠለፍ ዕድል ለማግኘትም በዌስትሀም እና በኢፕስዊች በውሰት አሳልፏል።
አዲሱ የሲቲ አለቃ ኢንዞ ማሬስካም የቅድመ ውድድር ዝግጅት ቡድናቸውን ሲያሳውቁ ፍሊፕስን ባለማካተት እንደማይፈልጉት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በኢትሀድ ያልተወደደው “የዮርክሻየሩ ፒርሎ” ለሲቲ ከፈረመው ስድስት ዓመት ውስጥ 4 የባከኑበት ሲኾን አሁንም በውሰት ውል ወደ ሸፊልድ ለማቅናት በር ላይ መቆሙን ዘ ሰን አስነብቧል።
✍️በንዋይ ሙሉጌታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here