የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽትም ቀጥለው ይካሄዳሉ።
በሊግ «ኤ» የምድብ ሦሥተኛ ጨዋታ፡ በሜዳዋ የምትጫወተው ክሮኤሺያ እንግሊዝን የምታስተናግድበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል። ክሮኤሺያ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ጨዋታዎች በስፔን ተሸንፋ፡ ቼክ ሪፐብሊክን በማሸነፍ በ3 ነጥብ በምድቧ 3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ተጋጣሚዋ እንግሊዝ በበኩሏ ቼክ ሪፐብሊክን አሸንፋ በስፔን ብትሸነፍም፡ በእኩል 3 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጣ 2ኛ ደረጃን ይዛለች። እንግሊዝ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፋ ነጥቧን ለማሳደግ ወደ ሜዳ የምትገባ ሲኾን፡ ሁለቱ ሀገራት የዓለም ዋንጫን ጨምሮ ባደረጓቸው ያለፉት ሦሥት ጨዋታዎች እንግሊዝ አሸናፊ ኾናለች። ጨዋታው ምሽት 1፡00 ላይ ይካሄዳል።
በዚሁ ምድብ ሁለቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ምድቧን የምትመራው ስፔን፡ ምንም ነጥብ የሌላትን ቼክ ሪፐብሊክን ምሽት 3፡45 ላይ ትገጥማለች።
በአሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፉኤንቴ የምትመራው ስፔን ላለፉት 40 ተከታታይ ጨዋታዎች አልተሸነፈችም። ይህን ድንቅ ግስጋሴዋን አስጠብቃ በተጋጣሚዋ ላይ ስንት ግብ ታስቆጥራለች የሚለው የብዙዎች ትኩረት ኾኗል።
በሌሎች የዛሬ ምሽት መርሐ ግብሮች፡ ሰሜን ማቄዶንያ ከስኮትላንድ፣ ስዊዘርላንድ ከስሎቬንያ፣ ቤላሩስ ከሳን ማሪኖ፣ ኤስቶንያ ከሉክሰምበርግ እንዲሁም አይስላንድ ከቡልጋሪያ ጋር ይጫወታሉ።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_23_2019_ዓ_ም
በዳናይት ሲሳይ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



