ውጤታማው አሠልጣኝ ኤዲሀው ከኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ተለያዩ።

0
67
እንደ ታዋቂው ጋዜጠኛ ዴቪድ ኦርንስታይን ዘገባ ኤዲሀው ከክለቡ ባለቤቶች እና አሥተዳደሩ ጋር ከተነሳው የተጫዋቾች ዝውውር አለመግባባት በኋላ እረፍት ለመውሰድ በመወሰናቸው ክለቡን ለመልቀቅ ፍላጎቱ እንዳላቸው አሳውቀው ነበር።
የ48 ዓመቱ እንግሊዛዊ አሠልጣኝ ኤዲሀው ከአምስት ዓመታት የኒውካስትል ቤት የአሠልጣኝነት ቆይታ በኋላ በስምምነት ተለያይተዋል።
አሠልጣኙ ቡድኑን ከተረከቡበት እ.ኤ.አ ከ 2021 ጀምሮ ከወራጅ ቀጣና በማትረፍ እ.ኤ.አ በ2025 የካርባኦ ዋንጫ አሸንፈው የክለቡን የ70 ዓመታት የዋንጫ ድርቅ ሰብረዋል።
በተጨማሪም ከ20 ዓመታት በኋላ ቡድኑን ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እንዲመለስ አስችለዋል።
ዘ ኒውዮርክ ታይምስ እንደዘገበው ጀርመናዊው የሳውዲው አል አህሊ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ማትያስ ጃይስሌ ኤዲ ሀውን በመተካት የኒውካስትል ዩናይትድ አሠልጣኝ ለመኾን ድርድር ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።
እንደ አንቶኒ ጎርደን እና ሳንድሮ ቶናሊ ያሉ ቁልፍ ተጫዋቾች ቡድኑን መልቀቃቸው ኤዲ ሀው ክለቡን እንዲለቁ በር መክፈቱ ተዘግቧል።
በአድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here