ቀይ ባሕር ለዓለም ንግድ እና ደኅንነት ወሳኝ የደም ሥር ከመኾኑም በላይ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሕልውና፣ የኀያልነት እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ትኩሳት ማዕከል ነው።

9

የኢትዮጵያ የባሕር በር አልባ መኾን በጂኦግራፊያዊ አጋጣሚ የተፈጠረ ሳይኾን ከጥንት ጀምሮ የነበራትን ቀጣናዊ መሪነት እና ባለቤትነት ለማዳከም በተቀነባበረ ውሥብሥብ እና ኾን ተብሎ በተጠነሰሰ የታሪክ ሴራ ምክንያት ነው።

ግብጽ እና ኤርትራ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባሕር እንዳትመለስ እና በውስጥ ሽኩቻ እንድትዳከም ከፍተኛ አቅም በማስተባበር ላይ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ የባሕር በር በነበራት ጊዜ ቀይ ባሕርን ከወራሪዎች እና ከወንበዴዎች በመጠበቅ ለቀጣናው ሰላም፣ ለዓለም አቀፍ ንግድ ደኅንነት እና ከአረቡ ዓለም ጋር ላለው ግንኙነት እንደ ድልድይ ኾና አገልግላለች።

ይሁን እንጂ ግብጽ ይህንን የኢትዮጵያን የበላይነት እና የውጭ ኀይሎች ተጽዕኖ ለመቀነስ ያደረገችው ጥረት የዘመናት ታሪካዊ ስትራቴጂ መኾኑን የመካከለኛው ምሥራቅ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሐጋይ ኤርሊች አረጋግጠዋል።

ግብጽ የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመቆጣጠር እንዲያስችላት፤ የውኃው ምንጭ የኾነችው ኢትዮጵያ በውስጥ ችግሮች የተዳከመች፣ ከባሕር በር የተገለለች እና ጠንካራ የባሕር ኀይል እና የኢኮኖሚ አቅም እንዳይኖራት በማድረግ ተፈጥሯዊ መብቷን እንዳትጠይቅ ማድረግ ላይ በጽኑ ታምናለች።

ግብጽ በቀጥታ ጦርነት ኢትዮጵያን ማሸነፍ ባለመቻሏ የውስጥ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ ስብጥሮችን በመጠቀም አማጺያንን በገንዘብ፣ በጦር መሣሪያ እና በዲፕሎማሲ በመደገፍ የውክልና ጦርነት ታካሂዳለች።

ይህ ስልታዊ ሴራ ኢትዮጵያ ሀብቷን በውስጥ ችግሮች ላይ ብቻ አውላ ዐይኗን ወደ ቀይ ባሕር እና ዓባይ እንዳታዞር ለማድረግ ያለመ ነው።

በዚህ ረገድ ኤርትራም ከግብጽ ጋር የሚጣጣም የራሷ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት አላት።

የግብጽ፣ የኤርትራ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ጠል ኀይሎች ዘመናትን የተሻገሩ ሴራዎች እና የውስጥ ግጭት የማቀጣጠል ጥረቶች ጊዜያዊ እንቅፋት ቢኾኑም የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ እና ጂኦ-ፖለቲካዊ ትንሣኤ ለዘላለም ሊያስተጓጉሉት እንደማይችል አሁናዊ እንቅስቃሴው በተግባር እያሳየ ነው።

✍️ ዘጋቢ ፦ ስማቸው አጥናፍ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#AMECO ​#RedSeaAccess ​#EthiopiaRising

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_18_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በስትራቴጂካዊ አቅጣጫ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ ነው።
Next article‎የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን እመርታ