“የመስኖ ልማት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

7

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የወቅታዊ የግብርና ልማት ሥራዎች አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

በግምገማ መድረኩ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በሜካናይዜሽን፣ በአፈር ለምነት፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ ክላሥተር፣ መስኖ ልማት እና ሌሎች ተግባራት ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ምርትን በፍጥነት በመሠብሠብ ወደ መስኖ ልማት መሸጋገር እንደሚገባም ገልጸዋል። ለተፈጥሮ ሀብት ሥራ ቦታን መለየት እና ቁሳቁሶችን ቀድሞ ማዘጋጀት እንደሚገባም ነው የተናገሩት። የውል እርሻ በተገቢው መንገድ ካልተሠራ ከግጭት ምንጭነት ባለፈ የተዛባ አሠራርን የሚያመጣ በመኾኑ በአግባቡ መምራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ መስፍን አበጅ (ዶ.ር) በመኸር ወቅት የተከናወኑ ሥራዎች ውጤታማ ኾነዋል ብለዋል። በ2018/19 የምርት ዘመን ከለማው 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር ውስጥ 39 በመቶ ሰብል መሠብሠቡንም ተናግረዋል።

በ2019 የምርት ዘመን በክልሉ 734ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ ነው ብለዋል። በመስኖ ልማት አርሶ አደሮች ዘመናዊ ግብርናን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በትኩረት ይሠራልም ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ታረቀኝ ጀምበሬ በዞኑ ሰብል ሠብሠባ እና የመስኖ ተግባራ በትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል። ኮምባይነርን በመጠቀም ምርት እየተሠበሠበ ስለመኾኑም ተናግረዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አህመድ ጋሎ ቴክኖሎጅን በመጠቀም በክላስተር ለማልማት ጥረት ተደርጓል ብለዋል። በዞኑ ሙዝ እና አቮካዶ በስፋት እየለማ መኾኑንም ተናግረዋል።

ዘመናዊ ግብርናን ተግባራዊ በማድረግ ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም በውይይቱ ተመላክቷል።

ዘጋቢ:- ዓለምነሽ ንጉሴ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleሆልዲንጉ ለችግሮች መፍትሄ መፍጠር ለሚችሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች 10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሊሰጥ ነው።
Next article‎ድምጽ ለሌላቸው ሕጻናት ድምጽ እንሁን – የሕጻን ቤተልሄም ኀይሉ ማኅበረሰብ አቀፍ የትብብር ጥሪ!