ሆልዲንጉ ለችግሮች መፍትሄ መፍጠር ለሚችሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች 10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ሊሰጥ ነው።

7

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የስታርታፕ ምህዳር ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን መቅረፍ የሚያስችል “ካማ” የተሰኘ መርሐግብር አስጀምሯል።

የሆልዲንጉ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ.ር) እንደገለጹት ይህ መርሐግብር ስምንት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያውያን “ሥራ ፈጣሪዎች ፣ ስታርታፖች እና የፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ሀገር በቀል መፍትሔዎችን እንዲያዳብሩ፣ በተግባር እንዲፈትሹ እና ወደ ገበያ እንዲያሸጋግሩ ዕድል የሚፈጥር ነው።

ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ መፍጠር ለሚችሉ ኢትዮጵያውያን ወጣት ስታርታፖች 10 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር መርሐግብር እነዚህ ስምንት የልማት ድርጅቶች የፈጠራ ባለሙያዎች መፍትሔ እንዲያመጡባቸው የሚፈልጓቸውን ተጨባጭ የንግድ እና የአሠራር ፍላጎቶች ይፋ እንደሚያደርጉም ዋና ሥራ አሥፈፃሚው ተናግረዋል።

​በአራት ዙሮች የሚተገበረው የ“ካማ” መርሐግብር የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ የሚያሳድጉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንዲበለጽጉ እና ተግባር ላይ እንዲውሉ ዕድል በመፍጠር ለ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030″ ግቦች መሳካት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተገልጿል።

​በስምንቱ የልማት ድርጅቶች ለቀረቡ ችግሮች ፈጠራቸውን ተጠቅመው መፍትሔ ለሚያመጡ ወጣቶች ሆልዲንጉ የገንዘብ እና የሙያ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል። በመኾኑም የመፍትሔ ሐሳብ ያላቸው ወጣት ስታርታፖች ከዛሬ ኅዳር 17/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 29/2019 ዓ.ም ድረስ ለመጀመሪያው ዙር መርሐግብር ማመልከት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎”የወጉንን ፈተናል፣ የወጉንን አቅፈን ለሀገር ሠርተናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“የመስኖ ልማት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)