‎#አንኳር

12

‎ኤርትራን በተመለከተ፦
‎
“‎የኤርትራ መንግስት ከተደበቀበት ወጥቶ ከማያውቅበት በራሳችን አውሮፕላን እየወሰድን ጎረቤት ጋር አገናኝተነዋል።

ይህን ያደረግነው በጋራ ማደግ እንደምንችል ስለምናምን ነው። ከኤርትራ መንግስት አብረን ለመልማት ከፍተኛ ጥረት አድርገናል።

ለምሳሌ ኤሌክትሪክ ስለሚቸገሩ እናስገባላችሁና በኢትዮጵያ ዋጋ ተጠቀሙ ብለናቸው ነበር። ነገር ግን የኤርትራ መንግስት አልፈለገም።

መንገድ፣ ወደብ በጋራ እንስራ ብለን ጠይቀን የኤርትራ መንግስት አልፈለገም። ምክንያቱ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ለጊዜው መንግስት ነው። ነገር ግን ልማት፣ እድገት የሚል ቋንቋ መዝገበ ቃላቱ ውስጥ የለውም።

ልማት ፈጽሞ አይገባቸውም። ይሄ የእነሱ ድክመት ነው። ሰሜን እዝ ሲጠቃ ያሳዩት የመልካም ጉርብትና ባህርይ ደግሞ ይመሰገናል።

ነገር ግን ችግሩ የተጀመረው ወደ ትግራይ በመግባት ወጣቶችን መግደል፣ መሰረተ ልማት ማውደምና መዝረፍ ሲጀምሩ ነው።

በመጨረሻም የፕሪቶሪያው ውል ሲፈረም የኤርትራ መንግስት ማኩረፍ ጀመረ። አሁን ከኤርትራ መንግስት የምንፈልገው ሁለት ነገር አለ፦
‎👉 አንዱ የኢትዮጵያን ጠላት ማስታጠቅ፣ ማስታጠቂያ መስመር መሆን፤ ለኢትዮጵያ ጠላቶች መተባባበር እንዲያቆሙ ነው።

‎👉ሁለተኛው ደግሞ ለጋራ ልማት አብረን እንሥራ። አብረን ስንሰራ ሃሳቡን፣ ገንዘቡንና ጉልበቱን እኛ እናዋጣለን። ተባባሪ ብቻ እንድትሆኑ ነው የምንፈልገው። ይህን ማድርግ ከቻላችሁ በሰላም አብሮ መኖር ይቻላል።

👉ነገር ግን ሻዕቢያ በማይታረም ስህተት ውስጥ የሚዳክር ሃይል ከሆነ ጥፋቱ ለኤርትራ ነው የሚሆነው።”
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous article‎መደመር ከኢትዮጵያ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ የሕልውና ሚዛን ፍልስፍና ነው!
Next article“ሻዕቢያ በማይታረም ስህተት ውስጥ የሚዳክር ኀይል ከኾነ ጥፋቱ ለኤርትራ ይኾናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)