
7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጥ ዲፕሎማሲን እንደምትተገብርም ተናግረዋል። በሱዳን ግጭት ወቅት ፓርቲዎችን በማስማማት የሽግግር መንግሥት እንዲፈጠር ኢትዮጵያ መሥራቷን ተናግረዋል። የሱዳን ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም በመኾኑ የሱዳን ሰላም እንዲመለስ አሁንም እንሠራለን ብለዋል።
ሱማሊያ እና ኬኒያን የደንበር ግጭት ባጋጠማቸው ወቅት ኢትዮጵያ በግንባር ቀደም አስማምታለች ነው ያሉት። የኤርትራ መንግሥት ከተደበቀበት ወጥቶ በራሳችን አውሮፕላን ወደ ጎረቤት ሀገር እየወሰድን ጎረቤት ሀገራት ጋር አገናኝተናል ነው ያሉት። ምክንያቱም ትልቅ አቅም አለ በጋራ ማደግ እንደምንችል ስለምናምን ነው ብለዋል።
ከኤርትራ መንግሥት ጋር አብረን ለመልማት ከፍተኛ ጥረት አድርገናልም ነው ያሉት። ኤሌክትሪክ፣ መንገድ እንሥራላችሁ ብንላቸው የኤርትራ መንግሥት አልፈለገም ብለዋል። የኤርትራ መንግሥት ልማት እና ዕድገት አይገባውም ነው ያሉት።
የፕሪቶሪያው ውል ሲፈጸም የኤርትራ መንግሥት ማኩረፉንም ገልጸዋል። አሁን ላይ ከሕገወጡ ሕውሃት ቡድን ጋር በመኾን የትግራይን ሀብት እየጫነ ወደ ኤርትራ መውሰዱንም ተናግረዋል።
✍️ለኤርትራ መንግሥት ምን መከሩ:-
የኢትዮጵያ ጠላት ማስታጠቂያ መሥመር መኾን እና ለጠላቶች መተባበርን አቁሙ ብለዋል። ለጋራ ልማት በሁሉም መስክ አብረን እንሥራ ነው ያሉት። ሀሳቡን፣ ጉልበቱን እና ገንዘቡን እኛ እናወጣለን እናንተ ተባባሪ ሁኑም ብለዋል።
ሻዕቢያ በማይታረም ስህተት ውስጥ የሚዳክር ኀይል ከኾነ ጥፋቱ ለኤርትራ ይኾናል ብለዋል። ኢትዮጵያ ለቀይ ባሕር ብላ ወረራ አትፈጽምም በሰላም እና በንግግር ነው የምንፈታው ነው ያሉት።
ዓባይ ለሁሉም ሀገራት የሚፈስ ነው፤ ቀይ ባሕርም እንዲሁ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ካላደገች እና ሰላም ካልኾነች ሰላም የሚኾን ቀጣና የለም፤ ኢትዮጵያ ትልቅ ዛፍ ናት ግንዳችን ከተጎዳ ሁሉም ይጎዳል ብለዋል።
የባሕር በር እንፈልጋለን መዝረፍ፣ መቀማት አንፈልግም በሰጥቶ መቀበል መርሕ አብረን ማደግ ነው የምንፈልገው፤ በምድርም፣ በሰማይም ተዘግተን ሰላም የሚኾን አፍሪካ እና ቀጣና የለም ብለዋል። ጦርነት አያስፈልግም ይቅርብን ፤ ለኤርትራ በሁሉም ነገር የኢትዮጵያን ያክል ማንም አይቀርባትም የኢትዮጵያ ዕድገት ማንንም አይጎዳም ብለዋል። ውጊያ ከተፈጠረ ግን ኢትዮጵያን ማንም እንደማያሸንፋት አረጋግጠዋል።
✍️ በያየህ ፈንቴ
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
