“ከ100 ሚሊዮን በላይ የሕዝብ ፍላጎት ከ10 ሺህ ባነሱ ግብር ከፋዮች አይሟላም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

12

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በግብር አሠባሠብ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና መፍትሄዎችን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አጠቃላይ ገቢ 454 ቢሊዮን ብር ኾኖ ወጪው 458 ቢሊዮን ብር መኾኑን ገልጸዋል። ከወጪው ውስጥ 88 ቢሊዮን ብር የሚጠጋው ለዕዳ ክፍያ መዋሉን ጠቁመዋል።

ከ100 ሚሊዮን የሚበልጠውን ሕዝብ ፍላጎት ከ10 ሺህ ባነሱ ግብር ከፋዮች ማሟላት አያስችልም። የሀገሪቱ ገቢ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) አንጻር ዝቅተኛ መኾኑ ተጨማሪ ገቢ ሳይሠበሠብ የልማት ሥራዎችን ማከናወን ፈታኝ ነው ብለዋል።

የግብርናው ዘርፍ ቢያድግም አርሶ አደሮች እስካሁን በቂ የሚባል ግብር እንደማይከፍሉ፣ ማዳበሪያ እና ዱቄት በወቅቱ እንዲደርስ ቢጠበቅም መሠረተ ልማቱን ለመገንባት የሚያስችል ግብር ከሌለ መንግሥት ኀላፊነቱን በበቂ ሁኔታ ለመወጣት እንደሚቸገር ገልጸዋል።

ሥራ የሚሠሩ እና ግብር የሚከፍሉ ዜጎች ግብር መክፈል ክብር እና ኩራት መኾኑን ሊገነዘቡ እንደሚገባም ገልጸዋል። ነጋዴዎች ግብር ከመክፈል ይልቅ መንግሥት በማይቆጣጠራቸው የተለያዩ የድጋፍ መንገዶች ብዙ ገንዘብ ሲያወጡ እንደሚስተዋል ጠቁመዋል።

ታማኝ ግብር ከፋይ ወሳኝ ቢኾንም አስበው የሚከፍሉ ጥቂቶች መኾናቸው እና አብዛኛው አካል በግብር ስወራ ላይ ጊዜ እንደሚያባክን ገልጸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ አሠራርን ማሻሻል እና ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚያስፈልግም አብራርተዋል።

✍️ ስማቸው አጥናፍ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article‎”ከነበርንበት የኢኮኖሚ አረንቋ ወጥተናል፣ ጉዞችን ትክክለኛ መኾኑን አውቀናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article#አንኳር