‎”በሞባይል ዋሌት 164 ሚሊዮን የሚጠጉ አካውንቶች ተከፍተዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

16

‎7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

‎‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አሁን ላይ በኢትዮጵያ ባንኮች ወደ 5 ነጥብ 3 ትሪሊዮን የሚጠጋ ተቀማጭ ሀብት መድረሱን ገልጸዋል።

‎‎70 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ብር” እና በሳፋሪኮም “ኤምፔሳ” መገልገል ችለዋል ነው ያሉት።

‎‎እያንዳንዱ ባንክ ባለው የዲጂታል ሲስተም በሞባይል ዋሌት 164 ሚሊዮን የሚጠጉ አካውንቶች ተከፍተዋል።

‎‎አጠቃላይ በዲጂታል ሲስተም በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሀብት ወደ 11 ትሪሊዮን ደርሷል ነው ያሉት።

‎‎ይህ በዲጂታል የሚንቀሳቀሰው ሀብት ላለፉት 70 እና 80 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከነበረው እንቅስቃሴ ጋር አይወዳደርም ነው ያሉት።

‎‎የዲጂታል ሲስተሙ በከፍተኛ ደረጃ የፋይናንሻል እንቅስቃሴው እንዲፋጠን እና ትርፋማ እንዲኾን ማገዙንም አንስተዋል።

‎‎በዚህም ምክንያት ባለፉት ሦሥት ወራት 426 ቢሊዮን ብር ለግል ሴክተሩ ብድር የተለቀቀ ሲኾን ይህም ከባለፈው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ጋር ሲወዳደር 62 በመቶ ዕድገት እንዳለው ገልጸዋል።

‎✍️ ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article“የጉባ ብሥራት ከንግግር ያለፈ በተግባር መሬት ላይ እየተሠራ ያለ ፕሮጀክት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየነዳጅ ድጎማው ማሻሻያ ይደረግበታል።