“የጉባ ብሥራት ከንግግር ያለፈ በተግባር መሬት ላይ እየተሠራ ያለ ፕሮጀክት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

21

7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድም (ዶ.ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የጉባ ብሥራት ሜጋ ፕሮጀክት የደረሰበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለምክር ቤት አባላት አብራርተዋል።

✍️1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ፦

1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት የመሬት እና የቴክኖሎጂ ዝግጅት ተደርጓል። የቱርክየ፣ የቻይ እና የኮሪያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ባለ 15 ፎቅ ሕንጻ ለመሥራት ሙከራ እየተደረገ ነው። በአንድ ወር ቪላ ቤት የሚገነቡ ፋብሪካዎችም እየገቡ ነው ብለዋል።

✍️የኒውክሊየር ፕሮጀክት፦

የኒውክሊየር ፕሮጀክትን ለመሥራት ተቋም መቋቋሙን ገልጸዋል። የቴክኖሎጂ መረጣ ተከናውኗልም ብለዋል።

✍️ የጋዝ ምርት፦

በሱማሌ ክልል የመጀመሪያ ፌዝ ጋዝ ማውጣት መቻሉንም ገልጸዋል። ለጋዝ የሚኾኑ ማደያዎች በአዳማ፣ ድሬድዋ እና አዲስ አበባ ላይ መገንባታቸውንም ነው የጠቆሙት። ፋብሪካዎች እና ተሽከርካሪዎች የጋዝ ምርትን እንዲጠቀሙ ተሠርቷል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዝ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች እንዲገነቡ እየተሠራ ነው። ፌዝ ሁለትን ወደ ግንባታ ለማስገባት ጥረት እየተደረገም ስለመኾኑ አብራርተዋል።

✍️ የማዳበሪያ ፋብሪካ፦

ለማዳበሪያ ፋብሪካ የተመረጠው ቦታ አለታማ በመኾኑ መሬቱን ለፋብሪካ የማመቻቸት ሥራ በመጠናቀቅ ላይ መኾኑንም ገልጸዋል። ማሽኖች በስፋት ገብተዋልም ነው ያሉት። የማዳበሪያ ፋብሪካው የአሞኒያ ፕላንት፣ የዩሪያ ፕላንት፣ ግራምሌሽን ፕላንት፣ የከረጢት ማሸጊያ ፕላንት ፋብሪካዎችን በስሩ መያዙንም ገልጸዋል። 3 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ፕሮጀክት እንደኾነም ነው ያስገነዘቡት። በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል።

✍️የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ፦

ፕሮጀክቱ በዘመናዊ መንገድ እየተሠራ ነው ብለዋል። አራት ሺህ የሚጠጉ ትራክተሮች በሰው ሠራሽ አስተውሎት ታግዘው እየሠሩ እንደኾነም ጠቁመዋል። መሬቱን የማዘጋጀት ሥራ ከሦሥት ወር ባነሰ ጊዜ ይጠናቀቃልም ነው ያሉት።

የጉባ ብሥራት ንግግር ሳይኾን በተግባር መሬት ላይ እየተሠራ ያለ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ይሠራልም ነው ያሉት።

✍️ በያየህ ፈንቴ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleየኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ በመጠናቀቅ ላይ ነው።
Next article‎”በሞባይል ዋሌት 164 ሚሊዮን የሚጠጉ አካውንቶች ተከፍተዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)