የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ በመጠናቀቅ ላይ ነው።

13

7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም ንግድ ድርጅት ለመግባት ከ20 ዓመታት ባላነሰ ጊዜ ስታደርግ የቆየችው ጥያቄ እና ድርድር አሁን ከሞላ ጎደል መጠናቀቁን ተናግረዋል።

በጥቂት ሀገራት የተያዙ ጉዳዮች መፍትሔ ሲገኝ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ገበያ ተጋሪ እንደምትኾንም አመላክተዋል።

በአሁኑ ወቅት 166 ሀገራትን ያቀፈው የዓለም ንግድ ድርጅት አብዛኛዎቹ አባል ያልኾኑ ሀገራት ወደ ድርጅቱ ለመግባት በድርድር ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

ድርድር ውስጥ የማይገኙ እና ወደ ዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት የማይቀላቀሉት ጥቂት ሀገራት ብቻ ስለመኾናቸውም ነው ያብራሩት።

የድርጅቱ አባል መኾን ለኢትዮጵያ ሰፊ የገበያ ዕድል እንደሚፈጥር እና ተገማች የኾኑ ፖሊሲዎች እንዲኖሩ በማድረግ በርካታ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለአፍሪካ የጋራ ንግድ ሥርዓት እንደ አንድ መንደርደሪያ ኾኖ እንደሚያግዝም አብራርተዋል።

✍️በስማቸው አጥናፍ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_17_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article#አንኳር
Next article“የጉባ ብሥራት ከንግግር ያለፈ በተግባር መሬት ላይ እየተሠራ ያለ ፕሮጀክት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)