
7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፦
በመንግሥት እና በግል ከ15 በላይ ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሀገሪቱ ተገንብተዋል
የአሰላ እና አይሻ የንፋስ፣ ገናሌዳዋ እና ሕዳሴ ግድብ፣ በገጠር የኮሪደር ልማቶች የተገነቡ የሶላር ፕሮጀክቶች የተመረቁ የኀይል ፕሮጀክቶች መኾናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን በሪፎርም በራስ አቅም በማሥተዳደር 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያስገኝ የነበረውን ወደ 43 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ተችሏል። 15 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ በራስ አቅም ተሠርተዋል። ከአዋሽ ኮምቦልቻ 100 ኪሎ ሜትር የባቡር ሀዲድ ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 210 ቢሊዮን ዶላር በመኾን በአፍሪካ ሦሥተኛው ኢኮኖሚ መኾን ተችሏል ነው ያሉት። በ2019 በጀት ዓመት ግብርና 7 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንዲያመጣ ይጠበቃል ብለዋል። በሀገሪቱ ዕድገት ላይ 31 ነጥብ 4 በመቶ መኾኑንም ተናግረዋል።
ኢንዱስትሪ 12 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት ይጠበቃል፣በሀገሪቱ ዕድገት ላይ 31 ነጥብ 8 በመቶ ይኾናልም ነው ያሉት።
በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 454 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል። 458 ቢሊዮን ብር ወጭ መኾኑንም ተናግረዋል። 88 ቢሊዮን ብር ገደማ ለዕዳ ክፍያ መዋሉንም ተናግረዋል።
ከዓመታት በፊት የመንግሥት ኩባንያዎች 17 ቢሊዮን ብር ግብር ይከፍሉ እንደነበር አንስተዋል። አሁን ላይ 376 ቢሊዮን ብር ወደ መክፈል አድገዋል ነው ያሉት። ዋና የኢትዮጵያ ግብር ከፋይ የመንግሥት ኩባንያዎች ናቸውም ነው ያሉት።
በሩብ ዓመቱ ከተሠበሠበው 454 ቢሊዮን ብር ውስጥ 153 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የተሠበሠበ ነው ብለዋል። የመንግሥት ኩባንያዎች 72 ሺህ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥረዋልም ነው ያሉት።
በያየህ ፈንቴ
#የመደመር_መንግሥት!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!