የባሕር በር ኢኮኖሚ ብቻ አይደለም፤ የብሔራዊ ደኅንነት በር ነው!

8

የባሕር በር ለሀገር ብሔራዊ ደኅንነት መጠበቅ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው። የባሕር በር ያላት ሀገር የራሷን የባሕር ኀይል በማቋቋም የባሕር ክልሏን እና ድንበሯን ከውጭ ጥቃት መከላከል ትችላለች።

ሀገር አስፈላጊ የሚባሉ ቁሳቁሶችን በሌላ ሀገር ፈቃድ እና ቁጥጥር ሳይገደቡ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ያስችላል። በአካባቢው የሚገኙ የባሕር ላይ መተላለፊያ መሥመሮችን መቆጣጠር፣ ሽብርተኝነትን፣ የባሕር ላይ ውንብድናን እና ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ወሳኝነት አለው።

በባሕር ጠረፍ ላይ የሚገኙ የራዳር እና የስለላ ጣቢያዎች ከባሕር ወይም ከአየር ሊመጡ የሚችሉ ጥቃቶችን ቀድሞ ለመለየት እና ለመመከት ይረዳሉ።

ወደብ ያላቸው ሀገራት ከሌሎች ኀያላን ሀገራት ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን ለማድረግ እና የጋራ የጸጥታ ትብብር ለመመሥረት ከፍተኛ የመደራደር አቅም እንደሚኖራቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የኢኮኖሚ እና የንግድ መቀላጠፍ ብቻ አይደለም። ይልቁንም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነትን ለማጽናት፣ ብሔራዊ ደኅንነቷን ለማስጠበቅ፣ በታሪካዊ ጠላቶቿ ሉዓላዊነቷ እንዳይደፈር አስተማማኝ ደኅንነትን ለመዘርጋት እና የቀይ ባሕርን ደኅንነት አስተማማኝ ለማድረግ የታለመ ነው።

የኢትዮጵያን ታሪክ መለስ ብሎ ለቃኘው በርካታ የባሕር በርን ታሥተዳድር በነበረበት ወቅት የቀይ ባሕርን ደኅንነት በማስጠበቅ የቀጣናውን ሰላም አስተማማኝ ማድረጓን ይመለከታል።

ዛሬም የባሕር በር ለማግኘት በጋራ ተጠቃሚነት የዲፕሎማሲ መርሕ ጥረት እያደረገች ነው። የባሕር ኀይልን መልሶ በማቋቋም ዝግጁ አድርጋለች።

ለቀጣናው ሰላም ዋስትና የሚኾነው የሀገር መከላከያ ሠራዊቷ ዘመኑን የሚመጥን የጦር ቴክኖሎጂ ታጥቋል። ዘመናዊ የጦር አውሮፕላኖች፣ ድሮኖች፣ ጀቶች እና ሌሎች የጦር ቴክኖሎጂዎችን እንዲታጠቅ እና እንዲጠቀምም አድርጋለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ሠራዊት የአፍሪካ ሀገራት በሚገጥማቸው ችግር ውስጥ ድንበር ተሻግሮ ሰላምን ለማስከበር የሚያስችል ብቃት ያለው አሥተማማኝ ሠራዊት ነው። ኢትዮጵያ የታጠቀቻቸው የጦር ቴክኖሎጂዎች ለቀጣናው ሰላም ዋስትና መኾኑንም ተናግረዋል።

✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_16_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article‎ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋ ዕውን እንዲኾን ሀሳቧን የምትሸጥበት መድረክም – ኮፕ 32
Next articleኢትዮጵያን መሪ እና አምራች የማድረግ ኀላፊነት የአሁኑ ትውልድ ነው።