
ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የኅብረተሰብ ጤና ጉባኤ እያስተናገደች በምትገኝበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ለውጦች ለአህጉሪቱ በተሞክሮነት አቅርባለች፣ እያቀረበችም ትገኛለች።
ተሞክሮዎቿም፦
✍️የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ወደ 86 ነጥብ 3 አድጓል
✍️ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ወደ 325ሺህ ገደማ ከፍ ብሏል
✍️የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ቅድመ መከላከልን ከሕክምና እና ከአዕምሮ ጤና አገልግሎቶች ጋር አቀናጅቶ እንዲሰጥ ሆኗል
✍️በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶች ሞት ከ100 ሺህ ሕጻናት ወደ 141 ዝቅ ብሏል
✍️ ከአምስት ዓመት በታች የኾኑ ሕጻናት ሞት ከ2016 እ.ኤ.አ ወዲህ ከ1 ሺህ ወደ 51 ቀንሷል
✍️በካንሠር ልየታ ባለፈው ዓመት ብቻ 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሴቶች የማኅፀን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ ምርመራ አድርገዋል
✍️በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች እና የሕክምና ግብዓቶች የገበያ ድርሻ 44 በመቶ አድጓል
✍️የኢትዮጵያ የመድኃኒት እና ክትባት ቁጥጥር ሥርዓት በዓለም ጤና ድርጅት የብቃት ደረጃ 3 ዕውቅና አግኝቷል
✍️ከ33 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በሥራቸው የያዙ 7 ሚሊዮን ገደማ አባዎራዎች የጤና መረጃ በዲጂታል እየተመራ ነው
✍️በ2018 ዓ.ም 35 ሚሊዮን ሰዎች የደም ግፊት እና 9 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰዎች የስኳር በሽታ ቅድመ ምርመራ ማድረግ መቻላየው እና ሌሎች ውጤቶች በጉባኤው በተሞክሮነት እየቀረቡ ይገኛሉ።
✍️ ዘጋቢ:- መሠረት መቅጫ
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#አዲስ_አበባ #ኅዳር_16_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
