ከአፍሪካዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ መፍትሔዎችን ማዘጋጀትና የመረጃ ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

6

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት፦

ዛሬ ከ5ኛው የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባዔ ጎን ለጎን ከዩጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተናል።

ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአፍሪካ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገትና የልማት ፈተናዎችን ለመፍታት ወሳኝ አቅም አለው።

ይህንን አቅም ለማሳደግ በራሳችን ቋንቋዎች፣ እውቀትና እውነታዎች ላይ የተመሠረቱ ቴክኖሎጂዎችን ማበልጸግ፣ የምርምርና የፈጠራ አቅማችንን ማጠናከር ይጠይቃል።

በጤናው ዘርፍም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የባለሙያዎችን አቅም በመደገፍና የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሻሻል ረገድ ጉልህ ሚና አለው።

ለዚህም ከአፍሪካዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣሙ መፍትሔዎችን ማዘጋጀትና የመረጃ ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂያችን እና በአዳዲስ የምርምርና የትምህርት ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ በመመሥረት፣ ከዩጋንዳና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር በቴክኖሎጂ፣ በጋራ ምርምርና በእውቀት ልውውጥ ያለንን ትብብር ማጠናከር ለጋራ ዕድገታችን ወሳኝ ነው።

Previous article‎ለጠላት የሚያስፈራ፣ በቴክኖሎጂ የረቀቀው የኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ዘብ!
Next articleየኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነትን ዕውን በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቷን ማረጋገጥ ይገባል።