
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሕዳሴ ግድብን በመረቁበት ወቅት ከጉባ ብሥራቶች መካከል የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እንደሚጀመር አብስረው ነበር።
ከፊት ለሚጠብቁን ግዙፍ ሥራዎች ታጥቀን እንነሳ፣ የኢትዮጵያን ልማት እናሳልጥ ማለታቸውም የሚታወስ ነው።
መንግሥት የአርሶ አደሮችን የማዳበሪያ ችግር ለመቅረፍ፣ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ እና ሀገሪቱ ለማዳበሪያ ግዥ የምታወጣውን በቢሊዮን ዶላር ለማስቀረት የገባውን ቃል ለመፈጸም ከሕዳሴ ግድብ ምርቃት ማግስት የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታን አስጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የማዳበሪያ ፋብሪካውን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት ተግተን እንሠራለን፤ ተግተን እንጨርሳለን ነበር ያሉት።
እነሱ ያወራሉ እኛ እንሠራለን፣ በሥራችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን ባሉት መሠረት የፋብሪካው ግንባታ በመፋጠን ላይ ይገኛል።
✍️አሁን የፋብሪካው ግንባታ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የጉባ ብሥራት የኾነው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል።
ለአጥር ግንባታ የሚያገለግሉ ግብዓቶች እየተመረቱም ነው። 223 የግንባታ ማሽኖችና ቁሶች ተገጣጥመው ወደ ሥራም ገብተዋል።
80 በመቶ የሚኾኑ ተሽከርካሪዎች በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ናቸው።
በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚገነባው ግዙፍ ይህ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያን የግብርና ግብዓት እጥረት በዘላቂነት በመፍታት ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው።
ፋብሪካው ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር እየተገነባ ይገኛል ።
በ74 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ በሚገኘው ፕሮጀክት ጠንካራ አለታማ መሬቶችን በማስተካከል የመሬት ዝግጅት ሥራዎች እየተሠሩ ነው።
እስካሁን 69 በመቶ የሚኾነው የቁፋሮ እና ተያያዥ ሥራ ተጠናቋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ40 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ምርት እንደሚገባ መናገራቸው ይታወሳል።
በዓመት እስከ 3 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የማምረት አቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የአርሶ አደሮችን የዘመናት የማዳበሪያ እጥረት ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመመለስ የፋብሪካው መገንባት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጵያ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የውጭ ምንዛሬ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካትም ያስችላል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_15_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
