ምክር ቤቱ በመጪው ሀሙስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት ጉባኤውን ያካሂዳል።

10

7ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ህዳር 17/2019 ዓ.ም ያካሂዳል።

በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተገኝተው ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26/2019 ዓ.ም ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ያቀረቡትን የዕቅድ ሪፖርት መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱም የመንግሥትን አቋም ካደመጠ በኋላ የድጋፍ ምላሹን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዕለቱ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ።

 

 

Previous article‎እንጅባራ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ኾነች።
Next article‎የዓለም አቀፍ መድረኮች መዳረሻ እና የጋራ ብልጽግናን እየገነባች ያለችው ኢትዮጵያ!