“ኢትዮጵያ የማይበገር እና ራሱን የቻለ የአፍሪካ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ ነች።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

22

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የCPHIA 2026 ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል።

ሙሉ መልእክቱ ቀጥሎ ቀርቧል፦ በአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) እና በኢትዮጵያ መንግሥት ትብብር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የCPHIA 2026 ጉባኤ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ።

በባሕላችን ሰላምታ የመልካም ጤንነት ምኞት ነው፤ በዚህም መንፈስ የአፍሪካ ኅብረት እና የአፍሪካ ሲዲሲ መቀመጫ ወደሆነችው አዲስ አበባ እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ኢትዮጵያ ባላት የሰው ኃይል፣ በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርት፣ በዲጂታል ጤና እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ኢንቨስት በማድረግ የማይበገር እና ራሱን የቻለ የአፍሪካ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ ነች።

በመደመር እሳቤ በመመራት፣ የጤና መዋቅራችንን በሦስት ዋና ዋና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ዙሪያ መለወጥ ይኖርብናል፤ እነሱም የሕክምና ልህቀት ማዕከላትን መገንባት፣ የአፍሪካ አምራቾችን ለማብቃት በጋራ ግዥ መፈጸም፣ እንዲሁም በታካሚዎች ጤና ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ጥብቅ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ናቸው።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የምታስተናግደውን የCOP32 ጉባኤ እንድትታደሙ በክብር ትጋብዛችኋለች። ቀጣይ አመት እንገናኝ!

‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

‎‎#Africa #CPHIA2026

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_14_2019_ዓ_ም

‎‎አሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article“አፍሪካ በዓለም ንግድ ውስጥ ለመወዳደር እሴትና ጥራትን ማሳደግ ይገባታል።” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next article‎​ለወገን ኩራት፣ ለወዳጅ የሰላም ዘብ፣ ለጠላት ረመጥ የኾነው የኢትዮጵያ መከላከያ