‎​ለወገን ኩራት፣ ለወዳጅ የሰላም ዘብ፣ ለጠላት ረመጥ የኾነው የኢትዮጵያ መከላከያ

4

‎የሀገር ጸጥታ እና ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ ኀላፊነት የተጣለበት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሕዝብ ማሕፀን ወጥቶ ለሕዝብ የሚቆም፣ የሀገርን አንድነት እና ክብር በደሙ የሚያስከብር የኩራት ምንጭ ነው።

‎‎የሠራዊቱ ማንነት የሚገለጸው ለወገኑ ኩራት፣ ለወዳጁ የሰላም ዘብ እና ለጠላቱ እሳት ኾኖ የሚፈራ በመኾኑ ነው። ይህም የሞራል ልዕልናው፣ የዲፕሎማሲ ወዳጅነቱ እና የወታደራዊ አቅሙ ማሳያ ናቸው።

‎‎ሠራዊቱ ጦርነትን የማይፈልግ፣ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ሰላምን ለማስጠበቅ የተገነባ፣ በተባበሩት መንግሥታት እና በአፍሪካ ኅብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ታሪክ ያለው የሰላም ኀይል መኾኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

‎‎ሠራዊቱ ከማንነቱ ጀምሮ የሕዝብ አካል ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዝኀነት የሚንጸባረቅበት፣ የብሔር ብሔረሰቦች እውነተኛ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ማሳያ ድንኳንም ነው።

‎‎ሠራዊቱ በሰላም ጊዜ የልማት፣ የዕውቀት ሽግግር እና የሰብአዊ ድጋፍ ባለቤት ነው። በችግር ጊዜም የሕዝቡን ደኅንነት ለማስጠበቅ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው።

‎‎የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የዜጎች የሰላም ዋስትና በመኾኑ ሕዝብ በሠራዊቱ ላይ ያለው እምነት የጸና ነው። ሠራዊቱ በየዘመኑ የከፈለው መስዋዕትነት የሕዝብን ከፍታ ያስጠበቀ እና ለወገኑ ሁልጊዜም አኩሪ ምዕራፍ ኾኖ የሚኖር ነው።

‎‎የሠራዊቱ ጥንካሬ በሉዓላዊነት ማስጠበቅ ብቻ ሳይኾን ከአህጉሪቱ እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጋር ባለው ሰላማዊ ግንኙነት ጭምር መኾኑን አረጋግጧል።

‎‎በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ያሳየው ዲሲፕሊን እና ጀግንነት ለአፍሪካ ቀጣና ሰላም ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ በወዳጆች ዘንድ ያለው ከፍታም ከሰላም ፍላጎቱ፣ ከሰብአዊ መብት አከባበሩ እና ከጋራ ተጠቃሚነት መርሁ ጋር የተቆራኘ ነው።

‎‎የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሰላም የቆመ ቢኾንም የሀገርን ዳር ድንበር ለመንካት የሚሞከርን ማንኛውንም ጥቃት የማምከን ጠንካራ አቅም ያለው ኀይል ነው።

‎‎በአጠቃላይ ሠራዊቱ በወታደራዊ ሥነ-ምግባር፣ በስልት፣ በቴክኖሎጂ እና በሞራል የዳበረ፣ ዘመናዊ ትጥቅ እና የሠለጠነ የሰው ኀይልን ያቀናጀ በመኾኑ የጠላትን ስሌት በማክሸፍ በድል የሚታወቅ ኀይልም ነው።

‎በስማቸው አጥናፍ

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

‎‎#AMECO #ENDF #National_Pride #African_Peacekeepers

‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_14_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article“ኢትዮጵያ የማይበገር እና ራሱን የቻለ የአፍሪካ የጤና ሥርዓት ለመገንባት ቁርጠኛ ነች።” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)