
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ዛሬ የአፍሪካ ንግድ ልማት ፎረም 2026ን በይፋ አስጀምረዋል።
አፍሪካ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ አምራች የሰው ኃይልና እያደጉ የመጡ ገበያዎች አሏት። ይሁን እንጂ ዋናው ፈተና ያላትን ሀብት በምን ያህል መጠን ወደ ሀገራዊና አህጉራዊ አቅም እየቀየረች ነው የሚለው ነው።
አፍሪካ ፀጋዎቿን በጥሬው ብቻ ከመላክ ባለፈ እሴት በመጨመር፣ በማቀነባበርና እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ከሀብቷ የሚገባትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለባት።
የአፍሪካ ምርቶች በጥራትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ፣ አህጉራዊ የጥራት መሠረተ ልማትን ማጠናከርና የጋራ የጥራት ሥርዓት መገንባት ወሳኝ ነው። ጥራት የንግድ እምነትና የገበያ ተወዳዳሪነት መሠረት ነው።
ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ የጥራት ተቋማቷን በአንድ ጣሪያ ሥር በማሰባሰብ፣ የምርቶቿን ጥራትና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ለማሳደግ እየሠራች ነው። ይህም “Made in Ethiopia” በሚለው ስያሜ የሚቀርቡ ምርቶች በየትኛውም ገበያ የጥራትና የእምነት መገለጫ እንዲሆኑ ያለመ ነው።
የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደታችንም የንግድ ሥርዓታችንን የበለጠ ተዓማኒና ተገማች ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ኢትዮጵያ በዚህ ጉዞ በተግባር ለአፍሪካ ማሳያ ለመሆን ቁርጠኛ ናት። አፍሪካ ያላትን እምቅ አቅም ወደ ተጨባጭ ብልፅግና ለመቀየር በጋራ መሥራት፣ የገበያ እምነትን መገንባትና የአህጉራዊ ንግድን ማስፋፋት ይጠይቃል።
#AfricaTradeForum2026 #MadeInEthiopia #QualityAfrica #Medemer
