
የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ዋና ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ፣ በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለውን 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) በማስተናገድ ዳግም የአፍሪካ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማዕከል ሆናለች።
“የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነት እና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነት እና ጽናት የሚደረግ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል፣ የሀገር እና የመንግሥት መሪዎች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የአፍሪካን የወደፊት የጤና ራዕይ ወደፊት ለማራመድ ምድረ ቀደምት በሆነችው ኢትዮጵያ ተሰባስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
