‎ታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለስፖርት ቱሪዝምና ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። ‎

9

በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር ዛሬ ተካሂዷል።
‎
‎በውድድሩ ከ60 ሺህ በላይ ሕዝብ ተሳታፊ ሆኗል። የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችና ዲፕሎማቶችም በውድድሩ ተሳትፈዋል።
‎
‎የታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራች ሻለቃ አትሌት ኀይሌ ገብረሥላሴ ታላቁ ሩጫ በተሳታፊዎች ቁጥርና በተቋም አደረጃጀት እያደገ መምጣቱን ተናግሯል።
‎
‎በዘንድሮው ውድድር ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታለቁ ሩጫ አጋር በመሆኑ በፋይናንስ ረገድ ካለው እገዛ በተጨማሪ የውድድሩን ደረጃ ከፍ ማድረጉንም አትሌት ኀይሌ ተናግሯል።
‎
‎ታለቁ ሩጫ በቀጣይ ተተኪ ትውልድ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ በመግለፅ በዘንድሮው ውድድርም ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች በባንክ ኦፍ አሜሪካ ድጋፍ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጿል።
‎
‎የተሳታፊዎች ቁጥጥር በጊዜ ሂደት እያደገ መምጣቱን በማስታወስም በቀጣዮቹ ዓመታት የተሳታፊዎችን ቁጥር 70 ሺህ ለማድረስ እቅድ መያዙን ነው አትሌት ኀይሌ ከዛሬው ውድድር በኋላ የተናገረው።
‎
‎የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው ታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለስፖርት ቱሪዝም ያለው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
‎
‎በርካታ የውጭ ዜጎችና ዲፕሎማቶች ተሳታፊ መሆናቸውን በማንሳትም ታላቁ ሩጫ ለሀገር ገፅና ግንባታ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል ሚኒስትሯ።
‎
‎ታላቁ ሩጫ ኢትዮጵያና አዲስ አበባ ታላላቅ ሁነቶችን በስኬት የማስተናገድ አቅም እንዳላቸው ለዓለም ማሳያ መድረክ መሆኑንም ጠቁመዋል።
‎
‎አትሌቲክስ የኢትዮጵያ ምድረ ቀደምትነት አንድ ማሳያ ነው ያሉት ሚኒስሯ ሰላማዊት ካሳ ሀገራችን የአትሌቶች ምድር መሆኗን ለዓለም ለማሳየትም ታለቁ ሩጫ ጉልህ አበርክቶ አለው ብለዋል።
‎
‎የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ውድድር ዛሬ ሲካሄድ በወንዶች ይስማው ድሉ ከአማራ ፖሊስ በሴቶች ደግሞ የኔዋ ንብረት አሸናፊ ሆነዋል።
‎
‎በወንዶች ይስማው ድሉን በመከተል ታደለ ሞሴ እና
‎ሮባ መርጋ 2ኛ ኦና 3ኛ ሆነው ጨርሰዋል።
‎
‎በሴቶች አልማዝ ዮሀንስ እና ዓለምነሽ ጥላየ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል።
‎
‎አሸናፊ አትሌቶችም 5 መቶ ሺህ ፣2 መቶ ሺህና በመቶ ሺህ ብር እንደየ ደረጃቸው ከታላቁ ሩጫ ተሸልመዋል
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous article60 ሺህ ተሳታፊዎች የተገኙበት 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በድምቀት ተካሄደ 🇪🇹
Next articleታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ🇪🇹