
በባንክ ኦፍ አሜሪካ የቀረበው የ2019 ዓ.ም 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር 60 ሺህ ተሳታፊዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በታላቁ ሩጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 60 ሺህ ሯጮችን ባሳተፈው በዚህ ውድድር፣ በአዋቂ ወንዶች ምድብ አትሌት ይስማው ድሉ በአንደኝነት አጠናቋል።
ይህም አትሌቱ ውድድሩን ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት እንዲያሸንፍ አስችሎታል።
በዚሁ ምድብ አትሌት ታከለ ሞሴ ሁለተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፣ አትሌት ሮባ መርጋ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
በአዋቂ ሴቶች ውድድር ደግሞ አትሌት የኔዋ ንብረት ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፣ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ እና አትሌት አለምነሽ ጥላዬ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
በውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች አንደኛ ሆነው ላጠናቀቁ አትሌቶች የ500 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ለወጡት ደግሞ በቅደም ተከተል የ200 ሺህ እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
