ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዲስ ክብረወሰን አስመዘገበ🇪🇹

17

ዛሬ በአዲስ አበባ በተካሄደው የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር 50 ሺህ ሰዎች ውድድሩን በመጨረስ ሜዳልያ ወስደዋል።

ይህም በዓለም የጎዳና ሩጫዎች ታሪክ ውድድራቸውን ጨርሰው ሜዳልያ የወሰዱ ሯጮች ክብረወሰን ሆኗል።

ከዚህ ቀደም በቦልደርባውልደር 10 ኪሎ ሜትር ውድድር በ47 ሺ 645 ተወዳዳሪዎች የተመዘገበ ነበር።

ሩጫዬ ቀለሜ በሚል መሪ ቃል የተካሄደው 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዩጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪ.ሜ ውድድር ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች ተካፍለውበት በድምቀት ተጠናቅቋል።

#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_13_2019_ዓ_ም
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous article‎ታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለስፖርት ቱሪዝምና ለሀገር ገፅታ ግንባታ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። ‎
Next article