የባሕር በር የኢትዮጵያ የሕልውና መሠረት ነው። 🇪🇹

3

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቋማት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሀገር እና ለሕዝብ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት እና ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ እንደ ሀገር ያስከተለውን ጉዳት በተመለከተ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ተቋማት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ብርሃኑ አማረ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከቀድሞ እስካሁን ኢትዮጵያን ከጠላት ሲጠብቅ መቆየቱን እና ዛሬም ጀግንነቱን እያሳየ መኾኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ምሁራን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

በዓለማቀፍ ደረጃ አምስት ቀጣናዎች እጅግ ስትራቴጅክ ቦታዎች መኾናቸውን ታደሰ ብሩ (ዶ.ር) በውይይቱ አንስተዋል። ከአምስቱ ሦሥቱ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ቀጣና የሚዋሰኑ መኾናቸውንም ጠቅሰዋል።

የስዊዝ ቦይ፣ ባብኤል መንደብ እና የሆርሙዝ ሰርጦች በዓለም ካሉ ስትራቴጂክ ቦታዎች ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቀጣናዎች በርካታ የዓለም ኀያላንን ትኩት የሳቡም ናቸው።

ኢትዮጵያ በዚህ ቀጣና ውስጥ እንደ መኖሯ በቀይ ባሕር የበለጠ ሚና እንዲኖሯት የባሕር በር ሊኖራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቀድሞ የሠራዊት አባላትም የባሕር በር ለኢትዮጵያ የህልውና መሠረት በመኾኑ ኢትዮጵያ በሴራ ያጣችውን የባሕር በር ማስመለስ የኢትዮጵያን ህልውና ማረጋገጥ ነው ብለዋል።
የቀድሞ የሠራዊት አባላቱ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንዲኖራት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉም ገልጸዋል።

✍️ ዘጋቢ፦ ተመስገን ዳረጎት

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹

#አዲስ_አበባ #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ጠዳ ከፍተኛ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለጤናው ዘርፍ መሻሻል የሚያግዙ ባለሙያዎችን እያፈራ ነው” ጤና ቢሮ
Next article‎ ጠላቶቿን ያሸበረው፣ ኀያልነቷን ያጸናው የኢትዮጵያ የድሮን ምርት!