“ጠዳ ከፍተኛ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለጤናው ዘርፍ መሻሻል የሚያግዙ ባለሙያዎችን እያፈራ ነው” ጤና ቢሮ

5

ጠዳ ከፍተኛ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ያሠለጠናቸውን 600 ተማሪዎችን አስመርቋል። ኮሌጁ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ይህ ለ22ኛ ጊዜ ነው።

ተመራቂ ድንቡሎ አምባው እና መሠረት ሲሳይ በሚድዋይፈሪ እና በፋርማሲ የትምህርት ክፍል አራት ነጥብ በማምጣት የሜዳሊያ ተሸላሚዎች ናቸው።

ከብዙ ድካም እና ልፋት በኋላ ለዚህ መብቃታቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል። ለዚህም ውጤታቸው በርትተው ማንበባቸው እና የቤተሰብ ያልተቋረጠ እገዛ ለስኬት እንዳበቃቸው አንስተዋል።

በተማሩበት ሙያ ማኅበረሰቡን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መኾናቸውንም ተመራቂዎቹ ገልጸዋል።

የተመራቂ ተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ልጆቻቸው ለጥሩ ውጤት እንዲበቁ እገዛ ሲያደርጉ መቆየታቸውንገልጸው ለምርቃት በመብቃታቸው ደስኞች መኾናቸውን ተናግረዋል።

የጠዳ ከፍተኛ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን ታደለ ማሩ ኮሌጁ ለ22ኛ ጊዜ 600 ተማሪዎችን በዲፕሎማ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ማስመረቁን አንስተዋል።

በፋርማሲ፣ በላብራቶሪ፣ በነርሲንግ፣ በሚድዋይፈሪ፣ በጤና ኤክስቴንሽን እና በጤና ኢንፎርማቲክስ የጤና ዘርፎች ኮሌጁ ማስመረቁንም ተናግረዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች 95 በመቶ መመዘኛ ፈተናውን ያለፉ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

ኮሌጁን ለማሳደግ እና የተማረ የሰው ኀይልን ለማፍራት በቀጣይ በትኩረት እንደሚሠሩም አንስተዋል።
ተመራቂዎች በቀጣይም ማኅበረሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሰው ኀይል አሥተዳደር ዳይሬክተር ምንትዋብ ማሬ የጠዳ ከፍተኛ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለጤናው ዘርፍ መሻሻል የሚያግዙ ባለሙያዎችን እያፈራ መኾኑን ገልጸዋል።

በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆችን ለማሳደግ በገንዘብም ኾነ በቴክኒክ በመደገፍ እየተሠራ መኾኑን አንስተዋል። ተመራቂ ተማሪዎች ሙያዊ ኀላፊነታቸውን ተረድተው በቅንነት እና በታማኝነት ማኅበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

✍️ ዘጋቢ፦ አምሳሉ አደራጀው

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!

#ጎንደር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleዓባይ ባንክ ከታክስ በፊት ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ።
Next articleየባሕር በር የኢትዮጵያ የሕልውና መሠረት ነው። 🇪🇹