
በዓለም ዙሪያ ያሉ ሀገራት የመከላከያ አቅማቸውን ለማዘመን ከፍተኛ በጀት በመመደብ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረቱ የጦር መሣሪያዎችን እያመረቱ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያም ከዘመኑ ጋር እኩል የሚራመድ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመገንባት ላይ ትገኛለች። ሠራዊቱ ከባሕላዊ የጦር መሣሪያዎች እንዲወጣ ተደርጓል፣ በራሱ አቅም የጦር መሳሪያዎችን እንዲጠግን እና መልሶ እንዲጠቀም ማድረግም ተችሏል።
ከውጭ ሀገራት የሚገዙ የጦር ቴክኖሎጂዎችን ከመግዛት ይልቅ ወደ ማምረት እንዲሸጋገር ተሠርቷል፣ እየተሠራም ይገኛል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ዘመናዊ ድሮኖችን በማምረት መጠቀም ጀምራለች። ኢትዮጵያ በራሷ ዲዛይን የተደረገ ድሮንን ታመርታለች።
የጦር ኀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዘመኑ የዲጂታል በመኾኑ ከዘመኑ ጋር እየዘመነ እንዲጓዝ መሠራቱን አረጋግጠዋል። ኢትዮጵያ ዘመናዊ ድሮኖችን በራሷ አቅም በማምረት ለቀጣናው ሰላም እየሠራችም እንደምትገኝ መግለጻቸው ይታወቃል።
ኢትዮጵያ የተለያዩ ድሮኖችን በማምረት ላይ እንደምትገኝ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ፤ ባንዳ እና ባዳ ባለበት አካባቢ አቅም ወሳኝ መኾኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በከፍተኛ ቁጥር እያመረተች እንደምትገኝም አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ ጠላቶቿን ያሸበረው፣ ኀያልነቷን ያጸናው የድሮን ምርቷ በቀጣናው ያላትን ደኅንነት የማስጠበቅ ኀላፊነቷን በብቃት እንድትወጣ አስችሏታል። በራስ አቅም የተገነባው ይህ አቅም ኢትዮጵያን ከሌሎች ጥገኝነት እንድትላቀቅ ያደረገ አኩሪ ድል ነው።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ! 🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_12_2019_ዓ_ም
✍️ በያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
