
በኮፕ31 እና በኮፕ31 ፕሬዚዳንትነት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር፣ የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) ከኮፕ31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ(ዶ.ር)፣ የኮፕ31 ፕሬዚዳንትነት በድርድሩ ያሳየውን አመራር በማድነቅ ግልጽና አካታች ሂደቱን፣ የመጀመሪያውን ውሳኔ ረቂቅ በቅድሚያ መለቀቁን እና እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል። ኢትዮጵያ ለተሳካ ውጤት ያላትን ድጋፍ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ኮፕ31 ለኮፕ32 መሰረት የሚሆን ጠንካራና ግልጽ ውጤት ይዞ እንዲጠናቀቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
የኮፕ31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪፊኬሽን ትግበራ አጀንዳ ለሰጠችው ድጋፍ አመስግነው፣ ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
በተጨማሪም አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ኮፕ32 የተሳካ እንዲካሄድ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
