
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በዓባይ ሸለቆ መካከል ስትመሠረት ኤርትራ የኢትዮጵያ አንድ አካል ነበረች።
የዛሬዋ ኤርትራ በኢትዮጵያ የታሪክ ዑደት ውስጥ የጋራ ታሪክ እና የባሕል ትሥሥር ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነበራት።
በታሪክ በተፈጠረ እጥፋት በውስጥ አላዋቂዎች፣ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች እና በውጭ ኀይሎች ሴራ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተነጥላለች። በካይሮ መንግሥት ተጸንሶ በካይሮ የተወለደው የሻዕቢያ መንግሥት ኤርትራን ለዘመናት አሥተዳድሯል።
የሻዕቢያ መንግሥት የኤርትራን የቀይ ባሕር ወደቦች ወደ ፍርስራሽነት ቀይሯል። በሀገሪቱ ሥልጣኔን ቀብሯል፣ ኋላ ቀርነትን አስፍቷል። ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና ምርጫን የኤርትራ ሕዝብ እንዳያውቅ አድርጓል።
ዘመናዊነት፣ ቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ ልማት፣ ዘመናዊ ፋብሪካ፣ ዲጂታል ሥርዓት እና ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ሥልጣኔ የኤርትራ ሕዝብ እንዳያውቅ የሻዕቢያ መንግሥት ሠርቷል። ዛሬ ሕዝቡ ስደትን እንጅ ሠርቶ መለወጥን በሀገሪቱ አያስብም።
ኤርትራ በዓለም ላይ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተደራሽነት ካላቸው ሀገራት አንዷ ናት። የሞባይል ዳታ አገልግሎት ለሕዝብ ክፍት አይደለም። ዜጎች ኢንተርኔት የሚያገኙት በጥብቅ ቁጥጥር ሥር ባሉ የኢንተርኔት ካፌዎች ብቻ መኾናቸውን ከሀገሪቱ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
የፋይናንስ ሥርዓቷ ኋላ ቀር ነው። ዘመናዊ የገንዘብ ማውጫ ማሽኖች፣ የሞባይል ባንክ ዝውውር በሀገሪቱ አይታወቅም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ይገበያያሉ።
የሻዕቢያ መንግሥት ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ መሠረተ ልማቶች በሀገሪቱ ቆመዋል።
ይህ ሁሉ ኋላቀርነት ግን የሻዕቢያ መንግሥትን አያስጨንቀውም ትኩረቱ ሁሉ በሌሎች ሀገራት ጣልቃ በመግባት ግጭቶችን መፍጠር እና ጎረቤት ሀገራትን ማዳከም ብቻ ነው።
የቀጣናውን እና የኢትዮጵያን ለውጥ የማይፈልገው የሻዕቢያ መንግሥት በኢትዮጵያ ለሚንቀሳቀሱ ባንዳዎች የሎጂስቲክ፣ የገንዘብ እና የጦር መሣሪያ በመደገፍ ግጭትን ለማበራከት ይሠራል።
በአንጻሩ ግን ኢትዮጵያ በታዳሽ ኀይል ልማት፣ በቴክኖሎጂ፣ በፋብሪካዎች፣ በኢንቨስትመንት አማራጮች፣ በዲጂታል ፋይናንስ፣ በግብርና፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ትጠቀማለች።
የሀገር መከላከያ ሠራዊቷ ድሮኖችን፣ ተወንጫፊ ጀቶችን፣ የጦር አውሮፕላኖችን፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን፣ ዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅ ይጠቀማል።
በአየር መንገድ፣ በቴሌ መሠረተ ልማቶች፣ በባቡር መንገዶች፣ በውኃ ግድቦች፣ በአረንጓዴ አሻራ ልማት ዘርፈ ብዙ ዕድገትን አስመዝግባለች። የኢኮኖሚ ዕድገቷም በየዓመቱ ስኬትን እያስመዘገበ ይገኛል።
ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጉባኤዎችን በማስተናገድም ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነቷን አጠናክራለች።
የሕዝብ አገልግሎቷ በዲጂታል ሥርዓት እየተመራ ነው። ብቁ እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ የዋጀ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እየተገነባም ነው። ለቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ዕድገትም እየሠራች ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ከቀጣናው ሀገራት ጋር በጋራ ለማደግ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሠራች መኾኑን በተደጋጋሚ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችው ዕድገት ጎረቤት ሀገራትን የሚነካ እና አስተሳስሮ በጋራ እንድናድግ የሚያስችል መኾን አለበት ነው ያሉት።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
