
በደቡብ የኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን፣ ድሬ ወረዳ ውስጥ ከያቤሎ ከተማ በስተደቡብ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ይህ ቦታ “የጨው ቦቄ ሶዳ” በመባልም ይታወቃል። ስሙ በኦሮምኛ “የጨው ቤት” የሚል ትርጉም ያለው ሲኾን በጥንታዊ የእሳተ ገሞራ ጉድጓድ ምክንያት የተፈጠረ የተፈጥሮ ሐይቅ ነው።
ሐይቁ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ሲኾን፣ የቦረና ማኅበረሰብ አባላት ለዘመናት በባሕላዊ መንገድ በመጥለቅ ጨው በእጃቸው እንደሚያወጡ የአካባቢው ነዋሪ አቶ ዋቆ ጢቃቲ ነግረውናል።
የጨው ሐይቁ በጥራት እና በአገልግሎት የሚለዩ ሦሥት ዋና ዋና የጨው ዓይነቶችን ያመርታል። እነዚህም ለምግብነት፣ ለከብቶች መኖነት እና ለባሕላዊ ሕክምና ጥቅም ላይ ይውላሉ።
መንግሥት ለዚህ ትኩረት በመስጠት እንዲደግፋቸውም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።
ከሐይቁ የሚወጡት ሦሥቱ ዋና የጨው አይነቶች “ኢልኮሌ” ተብሎ የሚጠራው ንጹህ እና ነጭ የምግብ ጨው፣ ከሐይቁ የታችኛው ክፍል ከጭቃው ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣው ጥቁር ጨው እና ከደረቀ በኋላ ጥቁር መልክ ያለው ለእንስሳት ምግብነት የሚውለው ናቸው።
በተለይ ለአርብቶ አደሮች ጠቃሚ የኾነው አልካላይን ወይም ሶዳ ሲኾን ይህ የማዕድን ጨው ለተለያዩ ባሕላዊ መድኃኒቶች እና ለከብቶች ጤና መጠበቂያነት ጥቅም ላይ ይውላል።
የሐይቁ መገኛ የኾነው የድሬ ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪ ስለሺ ግርማ በዚህ የጨው ስፍራ ፋብሪካ ቢገነባ ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልጸው፣ ለባለሀብቶች እና ለክልሉ መንግሥት ፕሮጀክቱ እና የልማት ጥያቄው መቅረቡን ተናግረዋል።
ባለሀብቶች ወደ ስፍራው መጥተው አንዲያለሙም ጥሪ አቅርበዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#አዲስ_አበባ #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:-አንዱዓለም መናን ከቦረና ያቤሎ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
