
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት፦
ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ምድረ ገነት ጠቅላላ ሆስፒታልን ጎብኝተናል።
ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የቆየው ይህ ግንባታ፣ ከስድስት ወራት በፊት በአዲስ ውል እንደገና ተጀምሮ ወደ መጠናቀቂያው ደርሷል።
ይህ ባለ አምስት ወለል ዘመናዊ የጤና ተቋም ግንባታ ሲጠናቀቅ ወረቀት አልባ የጤና መረጃ ሥርዓት የሚመራ ሲሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከሕክምና አገልግሎት ጋር በማቀናጀት የተሻለ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።
የጤና ተቋማትን በአቅም፣ በቴክኖሎጂና በአገልግሎት ማሳደግ ጤናማ ኅብረተሰብን ለመገንባት የምናደርገው ቁርጠኛ ጥረት አካል ነው።
