‎116 ዘመናዊ ካሜራዎች የተገጠሙለት የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዬም እውነታዎች!

12

‎በእግር ኳሱ ዓለም የሚታዩ ዘመናዊ ስታዲዬሞች የብዙዎችን ቀልብ ይስባሉ። በየጊዜው እየዘመኑ የመጡ የመጫወቻ ሜዳዎች የተመልካችን ቀልብ መሳባቸው አልቀረም።

‎‎በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ በስፔን ላሊጋ፣ በጀርመን ቡንደስሊጋ፣ በጣሊያን ሴሪኤ እና በሌሎች የሊግ ውድድሮች ላይ የሚታዩ ዘመናዊ ስታዲዬሞች የእግር ኳሱን ዓለም ቀይረውታል።

‎‎የእግር ኳስን የቱሪዝም ዕድገት፣ የኢኮኖሚ ጥቅም የተረዱ ሀገራት ዘመናዊ ስታዲዬሞችን ገንብተዋል። ለአብነት የእግር ኳስን የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ የተረዱ አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ የዓለም ክዋክብት የኾኑትን ክርስቲያኖ ሮላንዶን እና ሊዮኔል ሜሲን በማስፈረም የዓለምን ትኩረት ለመሳብ ሞክረዋል። ኢንቨስትመንታቸውንም አነቃቅተዋል።

‎‎ኢትዮጵያ የዘርፉን ጠቀሜታ በመገንዘብ ዓለማቀፍ ስታዲዬሞችን ለመገንባት እየሠራች ነው። ከዚህ ውስጥ ለኢትዮጵያዊያን ኩራት የኾነው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ደግሞ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን እያስተናገደ ነው።

‎‎በካፍ እውቅና ያገኘው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ከዓመታት በኋላ አህጉር አቀፍ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ጀምሯል። የብሔራዊ ቡድኑን በስደት ከመጫዎት አድኗል። ከ52 ሺህ በላይ ተመልካቾችን የሚይዘው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ምቹ ዘመናዊ የደጋፊ መቀመጫ ወንበሮች ተገጥመውለታል።

‎‎ስታዲዬሙ ጨዋታ ለመጀመር ሲቃረብ፣ በእረፍት ሰዓት እና ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በራሱን ሜዳውን እንደ ውጭ ሀገራት ሜዳ ውኃ ያጠጣል። ይህም ኳሷ በፍጥነት እንድትንከባለል እና የተጫዋቾችን ጉዳት ለመቀነስ ያስችላል።

✍️የስታዲዬሙ ዘመናዊነት

👉 በምሽት ጨዋታዎችን ለማካሄድ የሚያስችል ደረጃውን የጠበቀ መብራት ተገጥሞለታል

‎👉ራሱን የቻለ የተጫዎቾች፣ የደጋፊዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የክብር እንግዶች መግቢያ በር አለው።

‎👉እንደ አማራ ክልል ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መረጃ ስታዲየሙ ወደ 116 ዘመናዊ ካሜራዎች ተገጥመውለታል።

‎‎👉የተጫዎቾች መልበሻ፣ የአሠልጣኞች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የክብር እንግዶች እና የከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት መቀመጫ፣ አሳንስር፣ የሚዲያ ባለሙያ፣ የኳስ አቀባዮች፣ ካፍቴሪያ፣ የጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ እና የመጸዳጃ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ተገንብተዋል።

‎👉 የመጫወቻ ሜዳው የተፈጥሮ ሳር፣ ሜዳውን በራሱ ውኃ የሚያጠጡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች፣ መብራቶች፣ 108 ካሬ ስፋት ያላቸው ስክሪኖች፣ ምቹ የደጋፊዎች መቀመጫ ወንበሮች፣ 12 የደጋፊ መግቢያ በሮች፣ ጊዜያዊ የሕክምና ክፍሎችም ተሠርተውለታል።

‎‎ይህ ዘመናዊ ስታዲዬም የሀገር ኩራት ኾኗል። የባሕር ዳር ከተማን የቱሪዝም መዳረሻነት የሚያሳድግ፣ ኢንቨስትመንትን የሚያነቃቃ አማራጭም ነው።

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎‎#ባሕር _ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም

‎✍️ በያየህ ፈንቴ

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleየኢትዮጵያ የባሕር በር የባለቤትነት ጥያቄ አግባብ እና መብት ነው።
Next articleበቦረና የማኅበረሰቡን ሕይወት እንዲቀይሩ የተገነቡት 18 ሰው ሠራሽ ሐይቆች።