የኢትዮጵያ የባሕር በር የባለቤትነት ጥያቄ አግባብ እና መብት ነው።

9

ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማሳደግ እና ሀገራዊ ደኅንነትን ለማስጠበቅ የባሕር በር መሠረታዊ ጉዳይ እና አስፈላጊ መኾኑን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪዎች ገልጸዋል።

የባሕር በሩ ኢትዮጵያ ሉአላዊነቷን እንድትጠብቅ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቷን እንድታረጋግጥ እንደሚያግዛት ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ እና የድርድር አማራጮችን መከተል እንዳለበት የገለጹት ተማሪዎቹ ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት እንደነበረች ግንዛቤ በመፍጠር የየራሳቸውን ኀላፊነት እንደሚወጡም ተናግረዋል።

በጂንካ ዩንቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ምስክር ከተማ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የባሕር በር ባለቤት እንደነበረች ገልጸው የባሕር በሩን ያጣንበት መንገድ አግባብ ባለመኾኑ የባለቤትነት ጥያቄ መጠየቅ አግባብ እና መብት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የነበራትን የባሕር በር በፖለቲካ ሸፍጥ በማጣቷ አሁን የተነሳው ጥያቄ ተገቢ መኾኑንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን እውን ለማድረግ የተለያዩ አማራጮችን መጠቀም እንደምትችልም መምህሩ ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ሕግን በመከተል የባሕር በር ባለቤት መኾን እንደምትችልም አብራርተዋል።

የወደብ ጉዳይ የኅልውና ጉዳይ በመኾኑ መንግሥት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ማንኛውም ማኅበረሰብ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት ነው የተገለጸው።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር _ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleዘመናዊ ወታደራዊ ቁመና ያለው የድል ሠራዊት
Next article‎116 ዘመናዊ ካሜራዎች የተገጠሙለት የባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲዬም እውነታዎች!