ኢትዮጵያ በሞዛምቢክ ላይ ያላትን የአሸናፊነት ብልጫን ለማረጋገጥ…

2

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ 2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በዛሬው ዕለት ከሞዛምቢክ ጋር በባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እያካሄዱ ነው።

ሁለቱ ሀገራት ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ አራተኛ ግንኙነታቸው ነው። ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ኢትዮጵያ የበላይ ናት።

የሁለቱ ሀገራት የመጀመሪያ ግንኙነት እ.አ.አ በ1980 በዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ 3 ለ 2 አሸንፋለች።

በ2023 የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ግንኙነታቸውም ያለ ጎል ተለያይተዋል።

ማፑቶ ላይ በተደረገው የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ ደግሞ በከነዐን ማርክነህ ብቸኛ ጎል አሸንፎ ተመልሷል።

ኢትዮጵያ ይህንን የበላይነት ለማስቀጠል፣ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሚኖራትን ዕድልም ለማስፋት እየተጫወተች ነው።

በዚህ ጨዋታ ኳስን ተቆጣጥሮ ወደ ጎል ለመድረስ ጥረት ከማድረግ ባሻገር ጥሩ ለጎል የሚኾኑ ሙከራዎችን እያደረጉ ነው።

በስማቸው አጥናፍ

​#AFCON_Qualifiers ​#EthiopiaVsMozambique #BDR-Stadium #AMECO

Previous articleኢትዮጵያዊነት በዋልያዎቹ!
Next articleየአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ ቀረበ።