የአየር ንብረት ፋይናንስ ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ ቀረበ።

1

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር)፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ በሚያስፈልገው ደረጃ፣ በተደራሽ መንገዶች እና ለታዳጊ ሀገራት ቅድሚያ ፍላጎቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ እንዲቀርብ ጥሪ አቀረቡ።

በCOP31 በተካሄደው “ከዉጥን ወደ ተግባር፡ በዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ፣ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድ እና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ አማካኝነት የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ” በተሰኘው የከፍተኛ ሃላፊዎች ውይይት ላይ ሲናገሩ፣ ለታዳጊ ሀገራት የገንዘብ ድጋፍና የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ሀገራዊ ዉጥኖችን ወደ ተግባር ለመቀየር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሀብቶች በቂ በማይሆኑበት ጊዜ ትግበራ እንደሚዘገይ፣ ተጋላጭነት እንደሚባባስ እና በጋራ ጥረት ላይ የሚኖረው እምነት እንደሚዳከም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ COP32ን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ዝግጅት ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት፣ የአየር ንብረት ፋይናንስ ቤተሰብ ድጋፍን ጨምሮ በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሀገራት ፈንድ እና በልዩ የአየር ንብረት ለውጥ ፈንድን ለማጠናከር የተጀመረውን የሀብት ማሰባሰብ ጥረት በደስታ ተቀብለው፣ ኢትዮጵያ ከሁሉም አጋሮች ጋር ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

#COP31 #COP32Ethiopia #ClimateFinance #LandOfOrigins

‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም
‎
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous articleኢትዮጵያ በሞዛምቢክ ላይ ያላትን የአሸናፊነት ብልጫን ለማረጋገጥ…