
ባሕር ዳር ዛሬ በኢትዮጵያ እና በሞዛምቢክ የአፍሪካ ዋንጫ 4ኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ደምቃለች። ኢትዮጵያዊነትም ከፍ ብሏል።
ደጋፊው በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ደምቆ ወደ ስቴዲየሙ ገብቷል። ይህም የከተማዋን ነዋሪዎች ከፍ ያለ ሀገራዊ ፍቅር እና ስሜት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ዙሪያ እና በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው ድባብ የስፖርትን እውነተኛ አንድነት የሚያሳይ ነው።
አሁንም ደጋፊዎች ወደ ስቴዲየሙ እየተመሙ ያሉት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹን) ለመደገፍ ብቻ ሳይኾን ሀገርን በጋራ ከፍ የማድረግ ታላቅነታቸውን ለማሳየት ጭምር ነው።
በከበሮ ድምቀት እና በሀገራዊ መዝሙሮች የተሞላው አየሩ የኢትዮጵያውያን የደም ሥር ከእግር ኳስ ጋር የተሳሰረ መኾኑን የሚያረጋግጥ ነው።
ድምፃቸው እንደ አንድ ሕዝብ አስተጋብቶ “ዋልያዎቹ! ሀገራችን ከሁሉ በላይ ትቀድማለች!” የሚል መልዕክትን ያስተላልፋሉ።
ዛሬ ከሞዛምቢክ አቻቸው ጋር ለሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ ለዋልያዎቹ በድል አድራጊነት መንፈስ የሚስተጋባው ዜማ ተጫዋቾቻችን ከውጤት ባለፈ የሕዝባቸውን ፍቅር ይዘው ወደ ሜዳ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
ይህ ድጋፍ የብሔራዊ ቡድናችን የጥንካሬ ምሰሶ፣ የድል ማብሰሪያ እና የኢትዮጵያዊነት ሕያው ምስክርም ነው።
#AFCON_Qualifiers #EthiopiaVsMozambique #BDR-Stadium #AMECO
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
