
ባሕር ዳር የኢትዮጵያ የስፖርት ቱሪዝም ዋና መፍለቂያ እና የድምቀት ማዕከል መኾኗን በተከታታይ ባስተናገደቻቸው ዝግጅቶች አረጋግጣለች።
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከእረጅም ዓመት በኋላ ወደ ውድድር ሲመለስ:-
⚽️ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከሴኔጋል አቻው ያደረጉትን ጨዋታ አስተናግዷል።
⚽️ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባሕር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ የደርቢ ጨዋታም የሚረሳ አይደለም።
⚽️ ዛሬ ደግሞ ዋልያዎቹ ከሞዛምቢክ ጋር ወሳኝ ጨዋታቸውን ማድረግ ጀምረዋል። እነዚህ እና ቀጣይ የሚደረጉ ወሳኝ መርሐ-ግብሮች ከተማዋን የሀገሪቱ የስፖርት መዲና እንድትኾን ዕድል ይሰጣታል።
እየተደረጉ ያሉት ታላላቅ የስፖርት ኩነቶች የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስቴዲየም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሠረተ-ልማት ማሟላቱን የሚያሳዩ ብቻ ሳይኾኑ የከተማዋን ሁለገብ ገጽታ የሚቀይሩ ስትራቴጂካዊ ኩነቶች ናቸው።
በቅድሚያ የስቴዲየሙ መገኘት እና ተከታታይነት ያላቸው አህጉር አቀፍ እና ሀገራዊ ጨዋታዎች መስተናገዳቸው የባሕር ዳርን የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ትንሳኤ በግልጽ ማሳየቱ ባለፉት ጨዋታዎች ታይቷል።
ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር የሚመጡ በርካታ ደጋፊዎች፣ ተጫዋቾች እና የሥራ ኀላፊዎች ወደ ከተማዋ ሲገቡ የሆቴል፣ የትራንስፖርት እና የንግድ ተቋማት አገልግሎትን ይነቃቃል፤ ይህ ደግሞ ስፖርት ቱሪዝም ምን ያህል የአካባቢያዊ የገቢ ማግኛ መኾኑን በተግባር ይገልጣል።
በከተማው እየተተገበሩ ያሉት የተቀናጀ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የባሕር ዳርን ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ከዘመናዊ የከተማ ፕላን ጋር በማዋሃድ ውበቷን እጥፍ ድርብ አድርገውታል።
አረንጓዴ እና የለመለሙ አደባባዮች፣ የተስተካከሉ እና የጸዱ ሰፋፊ መንገዶች እንዲሁም የጣና ሐይቅ እና የዓባይ ወንዝ ዳርቻዎች ማራኪ ገጽታ፣ ለጨዋታ ከመጡት እንግዶች ጀምሮ በየዕለቱ ለሚመጡ ጎብኚዎች ልዩ ዕይታን ሰጥተዋል።
የስፖርት ድምቀቱ ከተማዋን በብዙ ሕዝብ ሲሞላት የኮሪደር ልማቱ ደግሞ የተገኘውን ሕዝብ በውበት እና በንጽህና ተቀብሎ በማስተናገድ ከፍ አድርጎታል።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#AFCON_Qualifiers #EthiopiaVsMozambique #BDR-Stadium #AMECO
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
