ከውጭ ገቢ ወደ ማምረት! የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ከፍታ በተግባር እያሳየ ነው!

7

የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በተግባር የገለጠው ካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጫና ማጣሪያ ፕሮጀክት ሥራ መጀመሩ ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ፣ ለኢንዱስትሪዎች መነቃቃት እና ለቀጣናዊ ትሥሥር ትልቅ ምዕራፍን ከፍቷል።

በካሉብ የጋዝ ማውጫና ማጣሪያ ኩባንያ የውጭ ክፍል የሥራ ሂደት ኦፕሬተር አስፋው ወርቁ የፕሮጀክቱን መጀመር አስመልክቶ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ውስጥ የነዳጅ ዋጋ መናር ትልቅ ጫና እንደነበረውና አሁን ላይ ጋዝ ማምረት መጀመሩ በትራንስፖርት ዘርፍ ትልቅ መፍትሔ አምጥቷል።

ከውጭ በዶላር የሚገባውን የነዳጅ ግዥ በጀት በመቀነስ ረገድም አሁን ላይ የሚደረገው የጋዝ ማጣሪያና ማከፋፈል ሥራ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል።

ነዳጅን ከምድር ውስጥ አውጥቶ በማጣራት እና በማጠራቀሚያ ኮንቴነሮች በመሙላት ለተጠቃሚው ማድረስ መጀመሩ የሀገራችንን የኢነርጂ ዋስትና አስተማማኝ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በማዕድን ሚኒስቴር የካሉብ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ቢሮ የፕሮጀክት ማኔጀር ታደሰ ሉሌ ኩባንያው ከገባው የውል ስምምነት ማጠናቀቂያ በኋላ ፕሮጀክቱን ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ በባለቤትነት እንደሚያስረከብ ገልጸዋል።

በዚህም የአካባቢው ወጣት ኢንጂነሮች በሂደት ቴክኖሎጂውን በመልመድ የሀገራቸውን የተፈጥሮ ሀብት በራሳቸው አቅም ማምረት እንዲችሉ እየተደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፕሮጀክቱ የተፈጥሮ ሀብት ማውጣት ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ ወጣቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚማሩበትና አቅማቸውን የሚገነቡበት ትልቅ የትምህርት ማዕከል ሆኗል።

በአካባቢው ከሚገኙ ወጣቶች መካከል አብዱልከሪም አብዱላሂ እንደገለጸው፣ ኩባንያው በንድፈ ሐሳብ የተማሩትን እውቀት በተግባር እንዲለማመዱና ለሀገራቸው ዕድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ሰፊ ዕድል ፈጥሮለታል።

ጸጥ ባለው የካሉብ ሞቃታማ ምድር ስር ከሚፈልቀው የተፈጥሮ ጋዝ ባሻገር፣ ትልቁ ሀብት ሀገሩን በእውቀት እና በክህሎት ማልማት የሚችል ትውልድ መፍጠር እየቻለ መሆኑ በፕሮጀክቱ በግልጽ እየታየ ስለመሆኑ የዘገበው ኢብኮ ነው።

#CalubGasProject #Ethiopia #NaturalGas #EnergySecurity

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article‎ሰዓቱ እየደረሰ ነው፤ የዋልያዎቹ ደጋፊዎችም ለድጋፍ ዝግጁ ናቸው።
Next article‎በስፖርት የደመቀች፣ በኮሪደር ልማት የተዋበች – ባሕር ዳር