
ዛሬ ጠዋት የCOP32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴን በመሰብሰብ አጠቃላይ የሥራ ሂደቱን ገምግመናል። ዝግጅቶችን ከፈትሽን በኋላም ሥራዎች የሚመሩበት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ሰጥቻለሁ። ጉባኤውን በስኬት ለማስተናገድ ሁሉም ግብረ-ኃይሎች ተናብበው እንዲሠሩ በማድረግ፣ የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አካሄድ መከተል ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት አሳስቤያለሁ።
COP32 ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከመሆኑ ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳን ለማራመድ፣ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እንዲሁም ብሔራዊ ጥረቶቻችንን ወደ ዘላቂ ውጤት ለመለወጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
