‎የመገጭ ግድብ እውነታዎች

8

‎💧የመገጭ ግድብ በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኝ የውኃ ማጠራቀሚያ እና የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ነው።
‎
‎🏗️ፕሮጀክቱ መጋቢት/2004 ዓ.ም በ4 ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውጥን ተይዞ ግንባታው ቢጀመርም ለ19 ዓመታት ቆሞ ቀር ኾኖ ቆይቷል።

ነገር ግን ከለውጡ መንግሥት ማግስት አቧራውን አራግፎ የተነሳ እና ለመመረቅ የበቃ ፕሮጀክት ነው።
‎
‎ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተመርቋል።
‎
‎የፕሮጀክቱ እውነታዎች፦
‎
‎👉 ውኃ የመያዝ አቅም 185 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር፣
‎
‎👉 የግድቡ ቁመት 76 ነጥብ 5 ሜትር፣
‎
‎👉 የግድቡ አናት ርዝመት 890 ሜትር ነው፣
‎
‎👉 የግንባታው አይነት (ሮክ ፊል ዳም) ይሰኛል።
‎
‎
‎🌱 ግድቡ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች፦
‎
‎🚜 መስኖ ልማት፦
‎ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን ያለማል።
‎
‎🚰ንጹህ የመጠጥ ውኃ፦
‎ ለጎንደር ከተማ እና ለአካባቢው ከተሞች የውኃ አቅርቦት ችግርን ይቀርፋል።
‎
‎🐟 ዓሳ ልማት፦
‎የዓሳ ምርትን ለማሳደግ ይጠቅማል።
‎
‎🏞️ ቱሪዝም፦ ሰው ሠራሽ ሐይቁ የመዝናኛ ስፍራዎችን ለማልማት ያግዛል።
‎
‎👷 ሥራ ዕድል፦
‎ለአካባቢው ወጣቶች እና ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያግዛል።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_07_2019_ዓ_ም
‎
‎በሙላት ክንፉ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleነገ ኅዳር 8/2019 ዓ.ም ዐይኖች ሁሉ ባሕር ዳር ላይ ናቸው!
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት