የግብጽ የኋልዮሽ ዘመን ናፋቂነት እና የኢትዮጵያ የድል ጉዞ

11

ግብጽ ከ85 በመቶ በላይ የሚኾነውን የዓባይ ውኃ ከኢትዮጵያ የምታገኝ በመኾኗ ይህንን የተፈጥሮ ሀብት እንደ ብሔራዊ ደኅንነት ጉዳይ አድርጋ ስትመለከተው ቆይታለች።

ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን በ1929 እና በ1959 የፈረመቻቸውን ስምምነቶች መሠረት በማድረግ ሌሎች የተፋሰስ ሀገራት በዓባይ ወንዝ ላይ የልማት ፕሮጀክቶችን እንዳይገነቡ በዲፕሎማሲ፣ በፋይናንስ ተቋማት እና በቀጣናዊ አለመረጋጋት ስትራቴጂዎች ስትከላከል ቆይታለች።

ይሁን እንጂ ራሷ የአስዋን ግድብን እና የቶሽካ ፕሮጀክቶችን ስትገነባ የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራት አላማከረችም፤ ይህም ከ100 ሺህ በላይ የሱዳን ኑቢያውያንን ማፈናቀሏ እና ታሪካዊ ቅርሶች እንዲቀበሩ ማድረጓን የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ.ር) ለግብጽ የራስ ወዳድነት አቋም ማሳያ አድርገውታል።

ግብጽ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እንዳይሰጡ በማድረግ፣ በዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ እንዳትጠቀም እና የልማት ፕሮጀክቶችን እንዳትሠራ አጥር ኾና ቆይታለች።

ኢትዮጵያ የውጭ ብድር እና ድጋፍ ሳይኖራት በራሷ አቅም የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን አጠናቃ ወደ ኀይል ማመንጨት ተሸጋግሯለች። ይህም ግብጽ በዓለም አቀፍ አበዳሪዎች በኩል ስታደርግ የነበረውን የዘመናት ዲፕሎማሲያዊ እና ፋይናንሳዊ ተጽዕኖ ዋጋ አሳጥቶባታል።

ኢትዮጵያ በፀጥታው ምክር ቤት እና በአፍሪካ ኅብረት መድረኮች ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የውኃ አጠቃቀም እንዲሁም ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ ዓለም አቀፍ መርሆዎችን በማስተጋባት የልማት ፍላጎቷን ዕውን አድርጋለች።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የኀይል እጥረቷን በመቅረፍ፣ የኢንዱስትሪ ልማቷን በማፋጠን እና ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኀይል በመሸጥ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን እየገነባች ትገኛለች።

#Ameco #AbbayRiver #Equitable_Utilization #Ethiopia

የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_06_2019_ዓ_ም

በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የሻቢያ የጥፋት ሴራ ከሽፏል፤ የኢትዮጵያ ኀያልነት ከፍታው ላይ ነው!”
Next articleየጎብኝዎችን ልብ በውበቱ የሚገዛው የሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ!