
ውበት እና ዘመን ተሻጋሪነትን የተላበሰው ባለግርማ ሞገሱ የባሕር ዳር አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ እውነታዎች፦
🌴 በልዩ ውበትና ኢንጅነሪንግ የተሠሩ ስምንት ምሰሶዎች አሉት።
🌴 እያንዳንዱ ምሰሶ ዘጠኝ በአጠቃላይ ደግሞ 72 ተንጠልጣይ መወጠሪያ የብረት ገመዶችን ይይዛል።
🌴 ወደ ድልድዩ ለመውጣትና ለመውረድ የሚያገለግሉ አራት የኮንክሪት አስፋልት ማሳለጫ መንገዶችንም የያዘ ነው።
🌴 በዘመናዊነቱ በአፍሪካ የቀዳሚነት ደረጃ ይዞ በ380 ሜትር ርዝመት እና በ43 ሜትር የጎን ስፋት ተገንብቷል።
🌴 በሁለቱም አቅጣጫዎች በአንዴ ብቻ 6 ተሽከርካሪዎችን ፈልሰስ አድርጎ ያስተላልፋል።
🌴 በሁለቱም አቅጣጫ ደረጃውን የጠበቀ የብስክሌት መንገድ አለው።
🌴እግረኞች የሚተላለፉበት ብቻ ሳይኾን ቆመው ጭምር ባለግርማው የዓባይ ወንዝ ከቤዛዊት ኮረብታ ጋር ተሰናስለው የፈጠሩትን ውበት ዙሪያ ገባ የሚመለከቱበት ሰገነትም አለው።
🌴 ይህን ዘመናዊ ድልድይ በምሽት ላየው ሰው ልዩ የመንፈስ ርካታን ያጎናጽፋል።
🌴 የድልድዩ ሙሉ ክፍል በተለያዩ እና በሚቀያየሩ የብርሃን ቀለሞች እንዲደምቅ በሚያደርግ “ወል ወሽ ላይት” በተባለ ቴክኖሎጂ የረቀቀ ነው።
🌴 ለዚህ የመብራት ቴክኖሎጂ ብቻ 111 ሚሊዮን ብር ወጭ ተደርጎበታል።
🌴 ውበቱ፣ የቱሪዝም ስበት አቅሙ፣ መዝናኛነቱ እና በአጠቃላይ ለባሕር ዳር ከተማና ለዓባይ ወንዝም ያላበሰው ግርማ ፋይዳውን አልቆታል።
🌴ይህ ድልድይ አንዱ የኢትዮጵያ ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶች ማሳያ ነው።
🌴 አኹን ደግሞ ከድልድዩ የሚነሳው እና መዳረሻውን ድባንቄ መዳኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ያደረገው የ7 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት የግንባታ ሥራ በመፋጠን ላይ ይገኛል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#Ethiopia #AMECO
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_05_2019_ዓ_ም
