‎ከፓን አፍሪካ እስከ ዛሬው የሰላምና የልማት ትሥሥር፦ የኢትዮጵያ አሕጉራዊ ተሰሚነት! 🌍

3

‎”ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ” የሚለው መርህ ከፓን-አፍሪካኒዝም እና ከፀረ-ቅኝ ግዛት ታሪክ የመነጨ ነው።

አፍሪካውያን የራሳቸውን ቀውሶች ከውጭ ጣልቃገብነት ነጻ በኾኑ ተቋማት እና በባሕል እውቀቶች እንዲፈቱ የሚያስችል አሕጉራዊ አቋም ነው።
‎
‎ኢትዮጵያ የዚህ ሐሳብ ቀዳሚ አቀንቃኝ ስትኾን የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ አቅም እና ያለውጭ ጣልቃገብነት መፍታት ይገባል የሚል አቋም አላት።
‎
‎ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መሥራች እና አስተናጋጅ እንደመኾኗ መጠን በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ላይቬሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ኮንጎ እና ሌሎች ቀጣናዎች ሰላም አስከባሪዎችን በማሰማራት እንዲሁም በኢጋድ ማዕቀፍ ውስጥ ግጭቶች በንግግር እንዲፈቱ በመተባበር ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለውን መርህ በተግባር አስመስክራለች።
‎
‎የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ እንዲታይ መደረጉ ኢትዮጵያ ለአፍሪካዊ መፍትሄ መርህ ያላት ቁርጠኝነት ማሳያ ነው።

ግብጽ ጉዳዩን ከአፍሪካ ውጭ ለማድረግ ያደረገችውን ጥረት በመመከት በአፍሪካ ኅብረት እንዲፈታ ማድረግ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል በመኾን የጋራ ተጠቃሚነት መርሆዋ ዓለም አቀፍ እምነት እንዲያገኝ አስችሏል።
‎
‎ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ውጭ ባሉ አካላት የሚደረጉ አላስፈላጊ ጫናዎችን በመቃወም የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን መታየት አለበት የሚለውን መርህ በጽናት የምትከተል መኾኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አረጋግጠዋል።
‎
‎የኢትዮጵያ አቋም አፍሪካውያን የውጭ ጣልቃገብነትን አስወግደው የአባቶቻቸውን ዕውቀት በመጠቀም ልዩነቶቻቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ የሚያደፋፍር ነው።

ይህ መርህ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ የዘለቀ ጥንታዊ አሕጉራዊ አቋም ነው።
‎
‎የኢትዮጵያ አቋም አፍሪካ ዘላቂ ሰላም እና ልማት የምታረጋግጠው በውጭ ሀገራት የመፍትሄ አማራጮች ጥገኛ በመኾን ሳይኾን በራሷ አቅም፣ በጋራ መከባበር እና በሰላማዊ ውይይት ችግሮቿን መፍታት ስትችል ብቻ ነው።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#Ethiopia #AMECO #AfricanSolutionsToAfricanProblems ​#AfricanPeace
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_05_2019_ዓ_ም
‎
‎✍️:-በስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleደቡብ ወሎ ዞን ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ቱሪስቶችን መሳብ ችሏል።