ደቡብ ወሎ ዞን ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ቱሪስቶችን መሳብ ችሏል።

2

የወሎ መሬት የታሪክ፣ የሃይማኖት፣ የባሕል እና የተፈጥሮ ጸጋዎች አምድ ነው።

ደቡብ ወሎ ከ300 በላይ ቋሚ፣ ከ11 ሺህ በላይ ተንቀሳቃሽ እና ከ100 በላይ የማይዳሰሱ ቅርሶች የሚገኙበት ቀጣና መኾኑን የዞኑ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ የቅርስ ጥበቃ እና ልማት ቡድን መሪ ይድነቃቸው ጌታነህ አረጋግጠዋል።

ሐይቅ እና አካባቢው፣ የቦረና ወረሂመኑ ብሔራዊ ፓርክ፣ መቅደላ አምባ፣ ግሸን ደብረ ከርቤ፣ ጀማ ንጉሥ፣ ወረኢሉ፣ ይስማ ንጉስ፣ ደገር ሸህዬ፣ ወለቃ ዓባይ ብሔራዊ ፓርክ፣ የአጼ ናኦድ ቤተ መንግሥት ከመዳረሻዎች መካከል ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።

የአምባሰል ሰንሰለታማ ተራሮችም የቀጣናው ውበት ማሳያዎች ናቸው።

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎች ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ 11 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን መሳብ ችለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ብቻ 2 ነጥብ 69 ሚሊዮን ጎብኝዎችን በማስተናገድ 2 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት ችለዋል።

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ እምቅ ሀብት ይዞ የቆየው ቀጣና የዘመናዊ መስተንግዶ እና የመሠረተ ልማት ክፍተት ነበረበት። ይህንን ክፍተት ለመሙላት እንደ ዞን በ20 ወረዳዎች 34 የመዳረሻ ቦታዎች ልማት ለማከናወን መለየቱን አመላክተዋል።

የሎጎ ሐይቅ ሪዞርትም በገበታ ለትውልድ ማዕቀፍ ውስጥ መገንባቱ የወሎን እምቅ የተፈጥሮ እና የባሕል ሀብቶች ከዘመናዊ መሠረተ ልማት ጋር በማስተሳሰር የሰውን ልጅ ሕይወት የሚቀይር እና የሀገሪቱን ገጽታ የሚገነባ ስትራቴጂያዊ የልማት ምዕራፍ ኾኖ ብቅ ብሏል።

የሎጎ ሐይቅ ፕሮጀክት እንደ ግሸን ደብረ ክርቤ ያሉ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ገዳማትን ከዘመናዊ መስተንግዶ ጋር በማገናኘት የቱሪዝም ክፍተትን የሚሞላ እና ክልሉን በታሪክ፣ በመንፈሳዊ እና በተፈጥሮ ቱሪዝም መስመሮች የሚያስተሳስር ታላቅ መሠረተ ልማት ነው።

የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት የወሎን ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ልዕልና ከዘመናዊ ቱሪዝም ጋር በማስተሳሰር የተፈጥሮ ሀብትን ወደ ኢኮኖሚ የሚቀይር እና ለትውልድ የሚተርፍ የዕድገት ምዕራፍም ነው።

የደቡብ ወሎ ዞን የቱሪዝም ዘርፍ ውጤታማ እንዲኾን መንግሥት እና ባለሀብቶች በቅንጅት ጠንክረው በመሠረተ ልማት አቅርቦት ላይ ሊሠሩ ይገባል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#DineForGenerations ​#LogoLakeResort #Ameco #VisitEthiopia

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_05_2019_ዓ_ም

✍️:- በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎ዘመናዊ ማሽኖች የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ከብክነት እያዳኑ ነው።