
21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የመደመር መንግሥት ዕሳቤዎችን መሠረት በማድረግ ይከበራል።
በዓሉ በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት “በብዝኀነት የደመቀች፤ በምክክር የፀናች ሥልጡን ኢትዮጵያ” በሚል መሪ መልዕክት በጅማ ከተማ ኅዳር 29/2019 ዓ.ም ይከበራል።
ይህንን አስመልክቶም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር በመኾን የመሪ ቃል ትንተና እያከናወነ ይገኛል።
በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ደስታ ሌዳሞ ሀገር በአንዴ እና በጥቂቶች አልተገነባችም ይልቁንም በትውልድ ቅብብሎሽ በተቀመጠ ጡብ እንጂ ብለዋል።
በመኾኑም የሚዲያ ባለሙያዎች ይህንን የሀገር ግንባታ የሙያ ሥነምግባርን በጠበቀ መልኩ እንዲያግዙም ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉ መከበር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለሀገሪቱ የብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋ እና ባሕል ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረጉ ተመላክቷል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#አዲስ_አበባ #ኅዳር_03_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
