‎🇪🇹የምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ ለሰው ልጆች ህልውና የዛሬው አርአያነት!

8

የሀገር ሉዓላዊነት ዳር ድንበርን ከማስከበር ባለፈ የተፈጥሮ ሀብትን በመጠበቅ ጭምር የሚረጋገጥ ነው።

ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 56 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው ትልቅ የአካባቢ ጥበቃ ድል ዓለም አቀፍ አድናቆትን አትርፎላታል።
‎
‎የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ፕሮግራም (UNEP) እንዳረጋገጠው የአረንጓዴ አሻራው ሁለገብ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በማከናወን ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን በብቃት እንድትወጣ አድርጓል።
‎
‎ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ በአረንጓዴ ልማት ጎዳና በመጽናት የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በመተካት ጭስ አልባ የትራንስፖርት ዘርፍ ለመፍጠር የጀመረችው ግዙፍ እንቅስቃሴ ለቀጣይ ዘላቂ ልማት ያላት የማያወላውል ጽናት ማሳያ ነው።
‎
‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “የታዳሽ ኀይል ልማትን፣ ዘላቂ የከተማ ግንባታን እና የአየር ንብረት ተስማሚ መፍትሄዎችን በስፋት እያሳደግን እንገኛለን” በማለት ሀገሪቱ ለማይበገር የአየር ንብረት ለውጥ ግዙፍ እንቅስቃሴ ውስጥ መኾኗን አረጋግጠዋል።
‎
‎ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመዋጋት እያደረገቻቸው ያሉ ጥረቶች ሀገሪቱ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ በር ከፍተዋል።

ይህም የሀገሪቱን በዘርፉ እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ንቅናቄ በማሳየት አጀንዳ ሰጭነቷን እና ቀዳሚነቷን ድጋሚ እንድታድስ ያደርጋታል።
‎
‎የኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት እና የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሽግግር ተሞክሮ በከፍተኛ የካርቦን ልቀት የሚታወቁት ያደጉት ሀገራት ከባዶ ቃል ወጥተው ሀብታቸውን እና ቴክኖሎጂያቸውን ለምድር መዳን በቅንነት እንዲያውሉ የኀላፊነት ጥሪ ይሰጣል።
‎
‎ኢትዮጵያ ከግዙፍ ኢኮኖሚ ማማ ላይ ለመድረስ ከምታደርገው ጥረት ጎን ለጎን፣ የአየር ንብረት ቀውስን ለመከላከል ከቃላት የዘለለ በተግባር የሰከነ እና ዓለምን ሊታደግ የሚችል አርዓያነት እያሳየች ትገኛለች።
‎
‎ኢትዮጵያ ዛሬ ለአየር ንብረት ለውጥ የምታደርገው ተጋድሎ የራሷን ሉዓላዊነት እና የዜጎቿን ደኅንነት ከመጠበቅ ባለፈ መላውን ዓለም ከከፋ የኢኮሎጂ አደጋ ለመታደግ የተዘረጋ እውነተኛ የድኅነት ድልድይ ነው።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#Ameco ​#ClimateAction ​#COP32 ​#SaveThePlanet #Ethiopia
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_03_2019_ዓ_ም
‎
‎✍️:- በስማቸው አጥናፍ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article‎ከቀይ ባሕር 1ሺህ ኪሎ ሜትር የባሕር ወሰን የምትጋራው ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋ የኅልውና ጉዳይ ነው !
Next articleኢትዮጵያ የአሸናፊዎች ሀገር ናት።